ፓለቲካ / ዜና
የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ላይ ቅሬታ እያሰሙ መኾኑን ተሰምቷል።
በትግራይ ቴሌቪዥን ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞች በፍርድ ቤት የተላለፈውን ውሳኔ ጣልቃ እየገባ ፍትሕን እያጓደለብን ነው ሲሉ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ላይ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡
የፌዴራሉ መንግሥት፣ በ2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል አቋቁሞት በነበረው ጊዜያዊ አስተዳደር ሥር “የሥራ ምድብ ተሰጥቷችኹ በብዙኀን መገናኛው ሲሰሩ ነበራችሁ” በሚል 40 የሚደርሱ ጋዜጠኞች ከሥራ ደረጃቸው ዝቅ ብለው እንዲሠሩ መደረጋቸውን የአሜሪካ ድምፅ ፅፏል፡፡
በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያቀረቡት 19ኙበፍርድ ቤት ወደ ሥራ ምድብ ቦታቸው እንዲመለሱ እንደተወሰነላቸው የገለጹት ጋዜጠኞቹ "ውሳኔው ግን አልተከበረም" ሲሉ ለቪኦኤ ቅሬታቸውን አሰሙተዋል ፡፡
የትግራይ ቴሌቪዥን አስተዳደር በበኩሉ "ሒደት ላይ ያለና ገና ያልተጠናቀቀ በመኾኑ፣ ማብራርያ ከመስጠት እቆጠባለሁ ብሏል፡፡
(ንጋት ፕሬስ)
