ቢዝነስ/ዜና
ሆላ ሀውሲንግ የተሰኘ አገር በቀል የሪልስቴት አልሚ ኩባንያ በአዲስ አበባ ከተማ በአራት ሳይቶች ዘመናዊ የመኖርያ ቤቶች ግንባታ መጀመሩ ተናግሯል።
ሆላ ሀውሲንግ ሪልስቴት ኩባንያው ይኽንን የተናገረው ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን የቤቶቹን ግንባታን ጨምሮ በተያያዥ ጉዳዬች ዙርያ አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
ሆላ ሀውሲንግ ሶልሽን የሪልስቴት ኩባንያ ከ7 ነጥብ 9 ሚልየን ብር በላይ መዋእለ ንዋይ ፈሰስ የተደረገባቸው ዘመናዊ የሚኖርያ ቤቶች በመዲናዋ አራት ሳይቶችላይ የሚገነባ መኾኑን የኩባንያው መስራችና የቦርድ ሊቀመንበር ነብዩ ዳንኤል ሲናገሩ ሰምተናል።
የቤቶቹ ግንባታ በሜክሲኮ ፣ጎተራ ፣ ባልደራስና ቡልቡላ አከባቢዎች በሚገኙ ሳይቶች ዘመን አፈራሽ የግንባታ ጥበብ የሚከናወን መኾኑንና ግንባታው ዓለማቀፍ የሪልስቴት የደረሰበት ደረጃና ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ የሚከናወን ነው ሲሉ የኩባንያው ኃላፊዎች ከጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ችለናል።
የኩባንያው መስራችና የቦርድ ሊቀመንበር ነብዩ ዳንኤል እንደገለጹት ከኾነም ቤቶቹ ከሁለት አመታት ተኩል ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለደንበኞቹ አስገንብቶ እንደሚያስረክብ የተናገሩ ሲኾን አሁን ላይ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየተስተዋለ ያለውን የመኖርያ ቤት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ብርቱ ጥረት እንደሚያደርግ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ።
በተለይም በመዲናይቱ እንደ ትልቅ ችግር ሆኖ እየተስተዋለ ያለው የፋይናንስ አቅርቦት ( ብድር) ችግር ሲኾን፣ ይኽንኑ ችግር ለመቅረፍም ሆላ ሀውሲንግ ሶልሽን ለደንበኞቹ እስከ 25 አመታት የሚቆይና የተራዘመ የብድር አቅርቦት ማመቻቸቱን ከኩባንያው መስራችና ማርኬቲንግ ዘርፍ ሐላፊ ዳግማዊ ጌታቸው ንግግር ተረድተናል ።
ሆላ ሀውሲንግ ሶልሽን በተለይም የመድህን ሽፋን ጋር በተያያዘም የኢንሹራንስ ሽፋኑን ሉሲ ኢንሹራንስ የተሰኘው ሀገር በቀል የመድን ኩባንያ ጋር አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።
ሌላኛው ፣ ከመግለጫው የሰማነው ኩባንያው ከፋይናንስ ጋር በተያያዘ ግሎባል ባንክ ጋር ስምምነት ተፈራርመዋል፤ በእለቱም መርኃ ግብርም በአብሮት መስራት የሚያስችላቸው የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸውን ተመልክተናል።
ኩባንያው በአዲስ አበባ ያለው የመኖርያ ቤት ችግር ለማቃለል የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልፆ፣ እንደ " ትዝታችን በኢቢኤስን" ጨምሮ በጣብያው በተለያዩ የመዝናኛ ዘርፍ ፕሮግራም በመሰራት የሚታወቀው ዮናስ ከበደ የሆላ ሀውሲንግ ሶልሽን አምባሳደር አድርጎ መሾሙን ተናግሯል ።
(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)



