የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከ1 ትሪሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር መከናወኑን አስታወቀ

 



የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከ1 ትሪሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር መከናወኑን ገልጿል ።


ባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ባለፉት ሦስት ወራት ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር መከናወኑ  እወቁልኝ ብሏል። 


ባንኩ የ2016 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ፅፏል። 


ባለፉት ሦስት ወራት አበረታች የዲጂታል የባንክ አገልግሎት የሥራ አፈፃፀም መመዝገቡ በዘገባው ጠቅሷል ፡፡ 


በባንኩ ዲጂታል አማራጮች በተከናወኑ ከ245 ሚሊየን በላይ የገንዘብ ዝውውሮች ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊየን በላይ የሆነ የብር መጠን መንቀሳቀሱን ከባንኩ የተገኘውን መረጃ ጠቅሶ ዘገባውን አሰራጭቷል ፡፡

 (ንጋት ፕሬስ)