የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል "ማለፊያ" የተሰኘው አዲስ አልበም የፊታችን ቅዳሜ ሊመረቅ ነው ተባለ

 



  Press release:- on the right side prom.&  journalist abreham gizaw 


 የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል "ማለፊያ" የተሰኘውን  አዲስ አልበም ምርቃት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2016 በሸራተን አዲስ ሆቴል ሊከናወን መኾኑ ሰምተናል።


የአልበሙን የምርቃት ሥነ- ሥርዓት አስመልክቶ ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 8/2016  ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ጋዜጣዊ መግለጫ ተስጥቶ ነበረ።





 ከመግለጫው የአልበሙ ምርቃት አሰመልክቶ ጥሪ የተደረገላቸው የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ የአርቲስቱ አድናቂዎች በተገኙበት እንደሚከናወን ተረድተናል ።


በሐግለጫው መድረኩ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል ከብላክ ፐርል ጋር የአርቲስት ማኔጅመንት ስምምነት መፈራረሙም መታዘብ ችለናል።


 በዚህም ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የሚሰራቸውን የሙዚቃ ኮንሰርቶች፣ የማስታወቂያ ሥራዎችን እንዲሁም የበጎ አድራጎት ሥራዎች ከብላክ ፐርል ጋር ቀሞያ አጋርነት እንደሚሰራ የብላክ ፐርል አዘጋጆች አረጋግጠዋል።


የበርካታ ግጥምና ዜማ ደራሲ የሆነው ተወዳጁ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አበበ የታላቁ የዜማ ጥበብ ባለቤት የሱራፌል አበበ ልጅ መኾኑ ይታወቃል።


የሙዚቃ አልበም ከብላክ ፐርል ባርና ላውንችና ከኤላ ቴቪ (ela tv) ጋር በመተባበር በቅርቡ ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል። 



              Photo: journalists 


"ማለፊያ" በውስጡ አሥራ ኹለት የሙዚቃ ሥራዎች  ይዟል። 



አልበሙ ነሐሴ 14/2015 በኤላ ሪከርድስ በኩል ለገበያ የቀረበ ሲሆን፤ አልበሙ በኹሉም ዲጅታል የሙዚቃ መሸጫ ፕላት ፎርሞች መለቀቁ በመረጃው ተጠቅሷል። 


(ንጋት ፕሬስ ~ አማኑኤል ክንደያ)