በኦሮሚያ ክልል የሌጲስ ቱሪዝም መንደር በዓለም ቱሪዝም ድርጅት የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ተብሎ ተመረጠ

 ቱሪዝም / ዜና


State minster of tourism, selshi girma 

በኦሮሚያ ክልል የሌጲስ ቱሪዝም መንደር በተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ተብሎ መመረጡን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡


የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ከኢትዮጵያ የቱሪዝም መንደሮች መካከል በማወዳደር ሰባት የሚሆኑትን ለተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት መላኩን ገልፀዋል።


የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ከቀረቡለት መንደሮች መካከል በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የሌጲስ ቱሪዝም መንደር ተመራጭ መሆኑን ተናግረዋል።


Oromia tourism comission comissioner Lelesi duga 


በቀጣይም የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማጥናትና በማወዳደር ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኙ የማድረግ ሥራም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።


በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የጮቄ ተራራ እና ወንጪ የቱሪዝም መንደር በዓለም ድንቅ መንደርነት የተመዘገበ መሆኑን አስታውሰው፤ የሌጲስ መንደር ሦስተኛ ድንቅ የቱሪዝም መንደር በመሆኑ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ እድገት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ገልፀዋል።


የሌጲስ መንደር ከቀርከሃ በሚሰሩ የእደ-ጥበብ ውጤቶች በስፋት የሚገኙበት፣ በአስደናቂ ፏፏቴ፣ አዕዋፋትና በርካታ የዱር እንስሳትም ይገኙበታል፡፡



የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ከሁለት ዓመት በፊት ነበር በተለያዩ አገራት የሚገኙ የቱሪዝም መንደሮችን አወዳድሮ እውቅና መስጠት የጀመረው፡፡


(ንጋት ፕሬስ)