የአፍሪኤግዚም ባንክ ለአፍሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ ድጋፍ ለማድረግ 1 ቢሊዮን ዶላር መመደቡ እወቁልኝ ብሏል


       የባንኩ  ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ካናዮ አዋኒ 



 የአፍሪካ ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም) የአፍሪካ የፊልም ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ አንድ ቢሊዮን ዶላር መድብያለሁ አለ።


የባንኩ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ካናዮ አዋኒ ባንኩ ይኽንን ያሉት በግብጽ በተካሄደው የአፍሪካ የንግድ ጉባኤ ምክክር ላይ ነው።


 የባንኩ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ካናዮ አዋኒ  የአፍሪካ ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ የአህጉሪቱን የፊልም ኢንዱስትሪዎችን አቅም ለማሳደግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ማለታቸውን አፍሪካ ትሪቡን ዋቢ አድርጎ ኢዜአ ፅፏል።


እ.አ.አ በ2022 ባንኩ ለአፍሪካ የሙዚቃ፣ ፊልም፣ ስፖርትና ሌሎች ኪነጥበባዊ ዘርፎች 600 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ይታወቃል።





ከወራት በኋላ በሚጀምረው የፈረንጆቹ አዲስ አመትም ለአፍሪካ ፊልም ኢንዱስትሪዎች በስቱዲዮ ግንባታ፣ ፊልም ቀረጻ እንዲሁም ለፊልም ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል አንድ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን የባንኩ ምክትል   ዋና ስራ አስፈጻሚ ካናዮ አዋኒ መናገራቸውን በዘገባው ተጠቅሷል ።


ለአብነትም በ2024 አየር ላይ ለሚውሉ የደቡብ አፍሪካ፣ ኬኒያና ናይጄሪያ ፊልሞች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አፍሪካን ትሪቡን አስነብቧል ።


በሴክተሩ የሚታየውን የመሰረተ ልማትና ቴክኖሎጂ፣ የገበያ ተደራሽነት እንዲሁም የብቁ ባለሙያ ችግርን ለመቅረፍ የአፍሪካ ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ እየሰራ እንደሚገኝ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው መናገራቸውን ናይጄሪያን ትሪቡን ዘግቧል።


የአፍሪካ የፊልም ኢንዱሰትሪ በየአመቱ ከጠቀላላ የሀገር ውስጥ ምርት 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የሚያስገኝ ሲሆን ከ5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል መፍጠሩን በመረጃው ተጠቅሷል።


(ንጋት ፕሬስ)