ገናን በሚሊኒየም አዳራሽ

 

ሸማች አምድ





የንግድ ትርዒት እና ባዛር ተከፍቷል ተባለ


ከ2000 በላይ አስመጪና ሻጮች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒት እና ባዛር  በቀን ከሰባት ሺህ በላይ ሸማቾች ይገኛሉ ተብሎ ይገመታል። ይኽ እንዲኽ እንዳለ በዝግጅቱ በየቀኑ በሀገራችን የሚገኙ ባህላዊ እና ዘመናዊ የሙዚቃ ባለሙያዎች ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ለሸማቹ እና ለጎብኝዎች ያቀርባሉ መባሉን ሰምተናል ፡፡ ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ ታህሳስ 11 ቀን እስከ ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ፤ ለ16 ቀናት የሚቆየው  "ገናን በሚሊኒየም "የንግድ ትርዒት እና ባዛር ቦሌ በሚገኘው ሚሊኒየም አዳራሽ  በይፋ መከፈቱን ተመልክተናል። ዝግጅቱ ለተከታታይ 16 ቀናት በሚቆየው የንግድ ትርዒት እና ባዛር ላይ አልባሳት፣ የስጦታ እቃዎች አቅራቢና አስመጪ፣ የምግብና መጠጥ ሻጮች ፣ የቤት ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች በአጠቃላይ ከበዓል ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ማንኛውም ግብዓቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብበት እንደሆነ  የተገለጸ ሲሆን 20 ለሚሆኑ ተቋማት ከክፍያ ነጻ በማድረግ የሚሰጡትን አገልግሎት እና ምርት እንዲያስተዋውቁ እድል መሠጠቱን በይፋዊ አዘጋጁ ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ገልጧል ። ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ በሀገራችን የተለያዩ ሁነቶችን (ኤቨንቶችን) በማዘጋጀት ሕጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ሲሆን ሥራውን በይፋ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አመታዊ በዓላት እና ሀገር አቀፍ ቀናትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ኤግዚቢሽን እና ባዛሮችን እንዲሁም የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን የሚያዘጋጅ ድርጅት መኮኑን ይታወቃል።


(ንጋት ፕሬስ )