ዜና/ መዝናኛ
አዲስ አበባ (ንጋት ፕሬስ) - ፌሽታ" የተሰኘ የሕፃናትና የወጣቶች የሚሳተፉበት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊከናወን ውጥን መያዙን ሰምተናል።
ዝግጅቱን ኤቫ ሌግዤሪ ሰርፕራይዝ ፕላነር የተባለ ተቋም የተዘጋጀ ሲኾን ታህሳስ 13 እና 14 2016 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል እንደሚከናወን የፕሮግራሙ አዘጋጆች ዛሬ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ተናግረዋል ።
ኤቫ ሌግዤሪ ሰርፕራይዝ ፕላነር የተለያዩ ዝግጅቶች በማዘጋጀት የሚታወቅ ድርጅት መኾኑንና በተለይም በዓይነታቸው ለየት ያሉ ኤቨንቶችን በማዘጋጀት በዘርፉ የካበተ ልምድ ያለው መሆኑን በመረጃው ተጠቅሷል።
ዝግጅቱ መጪውን የገና በአል አስመልክቶ የተዘጋጅ ነው። ልጆችና ወጣቶች የገና በአል ልዩ ልዩ ጨዋታዎችን ላይ እንዲሳተፉ የሚታደሙበትና እግረመንገዱም የአገራቸውን ቱባ ባህሎች የሚያውቁበት መርሐ ግብር እንዲኾን ተደርጎ ውጥን ተይዞለታል መባሉን ታህሳስ 05/ 2016 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል ለመገናኛ ብዙሐን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰምተናል።
በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ የሕፃናት እና ወጣቶች ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች ድርጅቶችን ጨምሮ የስጦታ ዕቃ አስመጪና ሻጮች፣ ምግብና መጠጥ አቅራቢዎች እንዲኹም በመዝናኛ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችና ተቋማት በግዮን ሆቴል በሚኖረው በዝግጅት ላይ እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ ከሰጡት መግለጫ መረዳት ችለናል።
ፌሽታ የተሰኘው በዚሁ የሕፃናትና የወጣቶች ዝግጅት (ፌስቲቫል) የተለያዩ ዘመን አፈራሽ የልጆች መጫወቻና መዝናኛዎች ይኖራሉ ተብሏል። በዝግጅቱ ላይ ለሚታደሙ ወላጆች ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅበትም።
ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በቴሌብር መተግበርያ በመጠቀም ፌሽታ የተሰኘው በዚሁ የሕፃናትና የወጣቶች ዝግጅት (ፌስቲቫል) ከ250 ብር ጀምሮ መግዛት ትችላላችሁ ተብላቹሀል።
(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)
-Advertsement-