ብሔራዊ ባንክ የትኞቹ የገንዘብ ፍሰቶችን ነው መቆጣጠር የፈለገው ?

 

             የምጣኔ ሐብት ባለሞያ አብዱልመናን መሐመድ



[በዚሁ ዙርያ የምጣኔ ሐብት ባለሞያው አብዱልመናን መሐመድ የሚሉት አላቸው]

በጣም ቀላል የሚመስል ግን ቀላል ያልሆነ ነገር እናንሳ። ከዋጋ ግሽበት ጋር በተያያዘ ብሄራዊ ባንክ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የገንዘብ መጠን እድገትን ይቆጣጠር (ብሄራዊ ባንክ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ይችላል አይችልም የሚለውን ክርክር ወደ ጎን ላድርገውና) በተደጋጋሚ ተብሏል። ዋናው ጥያቄው ገንዘብ ብዙ አይነት ስላለው የቱን ገንዘብ? የጥሬ ገንዘብ መጠን? የተንቀሳቃሽ ሂሳብ ገንዘብ መጠን? የተቀማጭ ሂሳብ ገንዘብ መጠን? ወይስ በጊዜ ገደብ የተቀመጠን ገንዘብ መጠን? ወይስ ሁሉንም? እ.አ.አ.2009 የታተመው የብሄራዊ ባንክ Monetary Policy Framework የዘረዘርኳቸው ላይ ሌሎች የገንዘብ አይነቶች ጨምሮ ለመቆጣጠር ታርጌት እንደሚያደርግ ያትታል። ሌሎች ሃገሮች ለመቆጣጠር ታርጌት የሚያደርጉት የገንዘብ አይነት ዝርዝር አላቸው። ብሄራዊ ባንክ ሊቆጣጠራቸው የሚፈልጋቸው የገንዘብ አይነቶች ላይ ጥያቄ ማንሳት ይቻላል። ለምሳሌ ጥሬ ገንዘብና በጊዜ ገደብ የተቀመጠን ገንዘብ (time deposit) በፍጹም አንድ አይደሉም።ጥሬ ገንዘብ በጣም ሊክዊድ ሲሆን በጊዜ ገደብ የተቀመጠን ገንዘብ financial asset ነው ማለት ይቻላል።ለለተለት ግብይት አንጠቀምበትም። እንደምውም ከጥሬ ገንዘብ ተነስተን  የዘረዘርኳቸው የገንዘብ አይነቶች በስኬል ብናስቀምጣቸው ሊክዊዲቲያቸው እየቀነሰ ይመጣል። አንድ የገንዘብ አይነት ዝቅተኛ ሊክዊዲቲ ካለው ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ ዝቅተኛ ነው። ስለዚህ ብሄራዊ ባንክ ዝቅተኛ ሊክዊዲቲ ያለው ገንዘብ ከከፍታኛ ሊክዊዲቲ ካለው  ጥሬ ገንዘብ ጋር እኩል ክብደት ተሰቶት እድገቱን ታርጌት ሊያደረግ አይገባም የሚል ክርክር ማንሳት ይቻላል። በጉዳዩ ላይ ያጠኑ ኢኮኖሚስቶች ለተለያዪ የገንዘብ አይነቶች  እንደ ሊክዊዲቲ መጠናቸው የተለያየ ክብደት በመስጠት monetary aggregation መሰራት አለበት ይላሉ። እንዴት ይሰራ ለሚለው ከቀላል የሂሳብ ቀመር እስከ ውስብስብ የሂሳብ ቀመር አለ።


(ንጋት ፕሬስ )