የአዲስአበባ ከተማ መምህራን ማህበር ሰራ የአስፈፃሚ አባላቱ ምርጫ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስመራጭነት አከናወነ



የምርጫ ስነስርዓት ሲደረግ ፡ ፎቶ አ/መ/ማ


በኢትዮጵያ የሚገኙ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ውስጥ በበብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ያከናወነ የመጀመርያው በሲቪል ማህበር የተቋቋመ ህብረት ለመኾን የሚያስችለው መርኃግብር መፈፀሙን ሰምተናል።


የአዲስአበባ መምህራን ማህበር ይኽን ያደረገው በኢትዮጵያ ያሉ ሲቪል ማህበራት ፍትሐዊ፣ ገለልተኛና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲለመድ በሚል ተነሳሽነት እንደኾነ ከማህበሩ ተናግሯል ።


በብዛት በኢትዮጵያ ያሉ በፍቃደኝነት የተመሠረቱ የሲቪል ማህበራት ዘንድ እየተደጋገመ የሚሰማውን የምርጫ ነክ ውዝግቦችን በኢፍትሐዊነት የሚነሱባቸውን ስሞታዎችን ማህበሩ እንዲቀረፍ ምሳሌ ለመኾን ውጥን ይዞ በመነሳት መኾኑን የመዲናዋ መምህራን ማህበር አስታውቋል ።


 የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር የመምህራን ማህበር እንደሀገር ከተሰጠው ተልእኮን ጨምሮ የተለያዩ ሞያዎች በማፍራት ረገድ ግንባር ቀደምነቱን በመጥቀስ ከሚጠበቅበት ኃላፊነት አንፃር በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አስፈፃሚ አባላቱን ምርጫ ማከናወኑን ተገቢነት ለጣብያችን አረጋግጠውልናል ።




የመምህራን ማህበሩ በ36ኛው በመደኛው ስብሰባው የስራ ሪፓርት በፕሬዝዳንቱ በኩል ያቀረበ ሲኾን በግንባታ ላይ ያለው የመምህራን ሆስፒታል የደረሰበትን ደረጃን ጨምሮ የማህበሩ የእቅድና ፕላን ጉዳዮች ዙርያ ለአባላቱ ማቅረቡ ታዝበናል።


የመምህራን ማህበሩ ከሰሞኑ የተለያዩ መርሐግብሮች ያከናወነ ሲኾን፣ ሴት መምህራን አቅም ማሳደግ ፣ በአገር ውስጥ ያለው የትምህርት አወቃወር ዙርያ ጥናታዊ ፅሁፎችን ጨምሮ በከተማዋ ያለው ትምህርት ቤቶች ያጋጠሙ ፈተናዎች ዙርያ የተለያዩ ሐሳቦችን ሲያነሳ ከቦታው ተገኝተን ለማወቅ ሠምተናል ።


በትምህርት ስርአቱ አቀራረፅ ዙርያ የአገር በቀል እውቀቶችን እንዲካተቱና የአገር በቀል እውቀቶች የትምህርት ሰርአቱ ለሚያፈራው ትውልድ የሚሰጠው ጥቅም በመረዳት ለመንግሥት የፓሊሲ ግብአት የሚኾን ሀሳቦችን አቅርበዋል።


በተለይም በትምህርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የሚመለከታቸው የትምህርት ዘርፍ ተዋናዮች አስፈላጊውን ውትወታ እንዲያደርጉ የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር መምህራን ማህበር በ36ኛ መደበኛ ጉባዔው ላይ ጥሪውን አቅርቧል ።


 አዲስአበባን ጨምሮ በአገራቀፍ ደረጃ ያሉ የኢትዮጵያ መምህራን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየገጠማቸው ያለው ማህበራዊ ቀውስና ችግሮች ዙርያ ለውይይት ቀርበው የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥቶባቸዋል።




በኢትዮጵያ አሁን ላይ እጅግ ፈተና እየኾነ የመጣውን የኑሮ ወድነት ለመምህራን ከአቅም በላይ እየፈተናቸው እንዳለ በመረዳት በመንግሥት በኩል መፍትሔ እንዲሰጥበት በመደበኛው ስብሰባ ላይ ተነስቷል።


ለዚህም መንግሥት አካላት አስፈላጊውንና አንገብጋቢን ጥያቄ መፍትሔ እንዲሰጡበት የአዲስአበባ መስተዳድር መምህራን ማህበር ጥሪውን አቅርቧል ።


በስብሰባው ተሳታፊ የነበረው ሌላኛው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ ባለስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቶም ነበር።


በተለይም የመምህራን የመኖርያ ቤት ፍላጎት የመምህራን ማህበሩ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት መንግሥት አስፈላጊውን መልስ እንዲሰጥበት መጠየቅን ጨምሮ ለመንግሥት የቀረቡ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥበት ተጠይቋል።




በተለይም በአገራቀፍ ደረጃ የመምህራን ቁጥር እየተመናመነ መምጣቱን ተከትሎ በትምህርት ስርአቱ ላይ መፃኢ ዕድል ላይ የተደቀነውን አደጋ ቀላል የሚባል እንዳልኾነ በጥናቱ ጠቁሟል። 


የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር የመምህራን ማህበር ከተመሠረተ ከሰብዓ አመታት በላይ ያለው እድሜ ጠገብ አንጋፋ ማህበር መኾኑን ሠምተናል።


(ለንጋት ፕሬስ  አማኑኤል ክንደያ)