ይድረስ_ለእቴቴ" የተሰኘው በወጣት ገጣሚት ሳምራዊት ደበበ የተፃፈ የግጥም መድብል በገበያ ላይ መዋሉን ሠምተናል።
አንዲት ሴት "ለእቴቴ" ለምትባል ወዳጇ የፃፈቻቸው የደብዳቤ ስብስብ ናቸው።
በህይወቷ ስላጋጠማት፣ ስለታዘበችው፣ ስለተደሰተችበት፣ ስለተከፋችበት፣ ስለልጅነቷ ስላላት ጥያቄዎች ለወዳጇ የፃፈችላትን ደብዳቤዎች ሸከፍከፍ ተደርገው የተፃፉ ግጥሞች መኾናቸውን አውቀናል።
ደራሲ ሳምራዊት ደበበ አሁን ላይ በኪነጥበቡ ዘርፍ ወደፊት እየመጡ የሚገኙ የተባ ብእር ካላቸው ወጣት እንስሳት ገጣሚያን ተርታ የምትመደብ ናት።
ገጣሚት ሳምራዊት ደበበ ለህትመት ያበቃችው ይኸው "ይድረስ ለእተቴ " የተሰኘውን መድብል ግጥሞች የህያው ስሜቶች ምስክር ናቸው የሚለውን አባባል የምታሟላ ባለ ልዩ ተሰጥኦ የስነፅሁፍ ሰው ናት።
በዚኹ የግጥም መድብል ጥበብ የገሀዱ አለም ነፀብራቅ መኾኑን ገጣሚዋ በህይወቷ የታዘበችውን፣ የተመለከተችውን ሁሉ በግጥሞችዋ ማሳየት የቻለች ብእረኛ እንደኾነች አስመስክራበታለች።
ይድረስ ለእተቴ የተሰኘውን የገጣሚት ሳምራዊት ደበበ የግጥም መድብል ዘመን አፈራሽ በኾነው የበይነ መረብ የመፅሐፍ ቋት "ኢትዮ ቡክስ ሪቪው" በተባለው መተግበርያ ለአንባቢያንና ለግጥም ወዳዶች እንካችሁ ብላለች።
የግጥም መድብሉ ግራፊክስ ጥበብ በኩሪ ግራፊክስ ድርጅት ተበጃጅቶ የቀረበ ነው።
ኩሪ ግራፊክስ በአገር ቤት አንቱታ ያተረፉ እንደ "ባልቦላ" ያሉ በፋና ቴሌቪዥን የሚተላለፈው ሴትኮም ድራማ ጥበቡን አስተዋፅኦ ያደረገ ተቋም ነው። የተቋሙ መስራችና ስራ አስኪያጅ አርቲስት ብሩክ መርዕድ ግራፊክስ ጥበብን ጨምሮ የሙዚቃ ባለሞያና የሙዚቃ ደራሲ ነው። አርቲስት ብሩክ መርዕድ እና ገጣሚት ሳምራዊት ደበበ ከአንድ ወንዝ የተቀዱ የጥበብ ሰዎች መኾናቸውን ተረድተናል።
ይድረስ ለእተቴን የተሰኘውን የግጥም መድብል ማንበብ ለምትሹ ሁሉ በተጠቀሰው መተግበርያ ገብታችሁ ግጥም እንድታጣጥሙ ተጋብዛችኋል ።
#ይድረስ_ለእቴቴ
https://www.ethiobookreview.com/book/yedres-le-etete-samrawit-debebe