ኪ ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶልሽን ለስልሳ ባለዕድለኞች አፓርትመንት ቤቶችን ማስረከቡ ተሰማ

 

ቢዝነስ/ዜና




ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶለሽን የተሰኘው አገር በቀል ቤት አልሚ ኩባንያ የመጀመሪያ ዙር እጣ ለእድለኞች አስረክቧል።


ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ከአሰራ አምስት ሺ ቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎቹ ለስልሳ (60) ባለእድለኞች የቤት ቁልፍ ማስረከቡ ተመልክተናል።


የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የበለፀገ ሶፍት ዌት በመጠቀም የወጣ ሲኾን ተአማኒነቱ በተረጋገጠ የዕጣ አወጣጥ ስነስርአት ስልሳ ለሚኾኑ ለቤት ፈላጊዎች የቤት ቁልፍ አስረክቧል።

 

 መርሐ-ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ በዲሊኦፖል ሆቴል ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ/ም 15,388 ከሚሆኑ የቤት ተመዝጋቢዎች መካከል 60 ለሚሆኑ ባለዕድለኞች  ዕጣ አውጥቶ ማስረከቡን ንጋት ፕሬስ ከቦታው ተገኝታ ታዝባለች። 


       photo; መሐል ላይ ግሩም ይልማ ስራ አስኪያጅ 


በዕጣ ከወጡት 60 አፓርተመንት ቤቶች  ውስጥ ሰላሳው (30) ባለ ሶስት መኝታ ክፍል ፣ ሃያ አንዱ(21) ባለሁለት መኝታ ክፍል እንዲኹም ዘጠኝ (9) ቤቶች ደግሞ ባለ አንድ መኝታ ቤቶች ናቸው ተብሏል።


ዕጣ የወጣላቸው አፓርትመንቶች በፒያሳ ፣በጋርመንትና በሐያት አከባቢዎች የሚገኙ አፓርትመንቶች ናቸው።


ለደንበኞቹ የተላለፉት አፓርትመንቶቹ ግንባታቸዉ ያለቀላቸው መሆናቸውን የኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ግሩም ይልማ ሲናገሩ ሰምተናል ።


ኩባንያው በ10 ዓመት ውስጥም 100 ሺ የመኖሪያ ቤቶች ለመገንባት ውጥን ይዞ እየተንቀሳቀሰ መኾኑን ተወርቷል።


ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች በ77 ሺሕ 280 ብር ቅድመ ቁጠባ በመቆጠብ የቤት ባለቤት መኾን የሚቻልበትን ፕሮጀክት ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንዳለ ተረድተናል።


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)



                    -Advertisements-