ኢንቨስትመንት ባንክ ስራው ምንድ ነው?

        photo:የካፒታል ማርኬት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዮ


[የምጣኔ ሐብት ዝግጅት]


ኢንቨስትመንት ባንኮች እንደ ሌሎች የንግድ ባንኮች ከሰዎች ላይ ተቀማጭ ገንዘብ አይወስዱም። የኢንቨስትመንት ባንኮች የማማከር ስራን የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ ኩባንያዎች የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ለመግባት ሲወስኑ ኩባንያውን ማዛጋጀት፣ ሼሩ ምን ያህል ነው የሚለውን መለየት ፣ ምን ያህል ሼር ለምን ያህል ሰው የሚለውን መለየት ስራዎችን ይሰራሉ። የካፒታል ገበያውን የሚቆጣጠረው አካል ፤ በካፒታል ገበያው ለሚሳተፉ አካላት ፍቃድ ከመስጠት እና ሂደቱን ከመቆጣጠር ባለፈ ኢንቬስተሮች በየትኛው ዘርፍ መሳተፍ አለባቸው የሚለውን አይወስንም ሃሳብም አይሰጥም ፤ ይህን የሚያደርጉት የአዋጭነት ትንተናዎችን በመስራት የኢንቨስትመንት ባንኮች ናቸው። ማማከር፣ ኢንቬስተሮችን እና ተፈላጊ የፋይናንስ ሃብት ማገናኘት የኢንቨስትመንት ባንኮች ስራ ይሆናል። የካፒታል ገበያ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶችን ወክለው ከሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያው ሆነ ከተቆጣጣሪ መ/ቤቱ ጋር በመሆን ብዙ ስራዎች ይሰራሉ። ለኢንቨስትመንት ባንክ መስረታ የሚጠየቀው ካፒታል ለንግድ ባንኮች ከሚጠየቀው ያነሰ ነው።

አሁን በኢትዮጵያ ስራ ላይ ያሉ የንግድ ባንኮች ጎን ለጎን የኢንቨስትመንት ባንክ ተሳትፎ የሚያደርጉበት እድል አላቸው። እንደ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን መረጃ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ መስጠት የሚጀምር ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ያሉና ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ባንኮችም የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠብቅ ተስፋ ተደርጓል።


Credit ፦

#DrBirukTaye (ECMA Director)