በአሜሪካ ኦህዮ ግዛት ይኖራሉ "አሚሾች" ይሰኛሉ፡፡
ፎቶ መነሳት፤ በጭራሽ! ከፍተኛ ቅጣት ከሚያስከትሉት የማህበረሰቡ ሕጎች ውስጥ አንዱ ፎቶ መነሳት ነው፡፡
ፎቶ መነሳት አንድን ሰው ራሱን አምላኪ እንዲሆን ይገፋፋዋል ብለው ስለሚያምኑ አይነሱም።
አልኮል መጠጣት፣ ትምባሆ ማጨስ፣ ዝሙት መፈፀም ሌሎች ከፍተኛ ቅጣት ከሚያስከትሉት ሕጎች ውስጥ ይጠቀሳል፡፡
አይፎንን በምታመርት ሀገር ውስጥ እየኖሩ ስልክ መጠቀምን እንደነውር ይቆጥሩታል፡፡
እነ ፎርድ፣ ኒሳን እና ቼቭሮሌት ያሉ ትላልቅ የመኪና ካምፓኒዎች ባሉባት ሀገር ዛሬም የሚጓጓዙት በጋሪ አሊያም በእግር ነው፡፡
በመብራት ባሽቆጠቆጠችው ሀገር ውስጥ ኤሌክትሪክን መጠቀም የማይታሰብ ነው፡፡
እንዲያም ሆኖ ግን ያለ ኤሌክትሪክ የሚሰሩት የእንጨት ስራ አንደኛ ተመራጭ ነው፡፡
መነሻቸው ከአውሮፓ ሲሆን በሃይማኖት ልዩነት ምክንያት ከስዊዘርላንድ የተሰደዱ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ ዋነኛ የገቢ ምንጫቸው የእርሻ ሥራ ሲሆን በእንጨት ሙያቸውም ይታወቃሉ፡፡
እንደ ስልክ፣ ላፕቶፕ፣ ቴሌቭዥን፣ መኪና ያሉ መሰል የቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን መጠቀም ምን አልባት በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅጣት ከሚያስከትሉ ተግባራት ናቸው።
እንደሚባለው እናት እና አባትን ጨምሮ መላው የማኅበረሰብ ክፍል የሚያገልበት ይህ ቅጣት በአሚሽ ዘንድ አስጨናቂው ቅጣት እንደሆነ ይነገራል፡፡
አሚሾች ሌላም አስገራሚ ሕግ አላቸው፤ ወጣቶች 18 ዓመት ሲሞላቸውና ክፉና ደጉን ማገናዘብ ችለዋል ብለው ሲያምኑ የውጪውን ዓለም እንዲያዩ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ከበዛ ለሁለት ዓመት፡፡
በዚያ ሁለት ዓመት ውስጥ ታዲያ ወጣቱ ከውጪው ዓለም ጋር ይተዋወቃል፡፡
ስልክ ይጠቀማል፣ መኪና ይነዳል፣ አልኮል ይጠጣል ሌላም ሌላም፡፡
ሁሉንም አይቶ ከጨረሰ በኋላ ግን ወደ ቀደመው ማኅበረሰብ መመለስ ከፈለገ በሁለት ዓመት ውስጥ መመለስ ይችላል፡፡
በሚያስገርም ሁኔታ ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት ሁሉንም ካዩ በኋላ ወደ ማኅበረሰቡ የአኗኗር ዘዴ ይመለሳሉ፡፡ ሲመለሱም በእምነታቸው መሰረት ይጠመቁና ይቀላቀላሉ፡፡
በአሚሽ ሕግ ፍቺ አይቻልም፡፡
ከጋብቻ በኋላ የትዳር ሕይወት ውስጥ የሚፈጠር አለመግባባት ካለ በአካባቢው ሽምግልና ይፈታል እንጂ መለያየት መፍትሔ ነው ብለው አያስቡም፡፡
ወንዶቹ ከጋብቻ በኋላ ፂማቸውን መላጨት አይችሉም ይባላል።
እነዚህን ለየት ያሉ ማኅበረሰቦች በዓመት እስከ 3 ሚሊየን የሚደርሱ ጎብኚዎች ይጎበኟቸዋል
