የአብነት ተማሪ ቤቶችን ለማቋቋም የሁለት አመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

 ዜና


      photo: በስካይላይት ሆቴል መግለጫ ሲሰጥ



ፕሮጀክቱን ያቋቋመው "ቁስቋም ቅድስት ማርያም መንፈሳዊ ማኅበር" ነው።


"በእንተ ስማ ለማርያም ለእኔ ተማሪ" ይሰኛል።  


በቁስቋም ቅድስት ማርያም መንፈሳዊ ማኅበር አማካኝነት የሚተገበር የሁለት አመት ኘሮጀክት ይፋ ተደርጓል።


በቁስቋም ቅድስት ማርያም መንፈሳዊ ማኅበር መጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን  ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ።


ለዘመናት የአገሪቱ የትምህርትና የእውቀት ስርዓት ሆኖ ያገለገለው የአብነት ትምህርት ለመታደግ የቀረበ ጥሪ በአዲስአበባ መጀመሩን ሰምተናል ።


በኢትዮጵያ በስፋት የእውቀት ማስተላለፍያ የሆነው የግእዝ ቋንቋ ለመታደግና ወደ ቀደመ ዝናውና ግልጋሎቱ እንዲመለስ ውጥን የያዘ የሁለት አመት ፕሮጀክት ነው ተብሏል ።


የአብነት ትምህርት ቤቶች በኢኮነሚ እጦት ሳቢያ እንደ  ቀደመው ጊዜ እየሆነላቸው ባለመሆኑ የተነሳ በርካታ ተማሪዎች እየተበተኑ እንዳሉ የዝግጅቱና የፕሮግራሙ አዘጋጅ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ማህበር ለመገናኛ ብዙሐን ተናግሯል ።


ይህ እንዲህ እንዳለ፣ እግረ መንገዱ የግእዝ ቋንቋ የመጥፋት አደጋ እየተጋረጠበት በመሆኑ ጥሪ ቀርቧል።


በኢትዮጵያ የግእዝ ቋንቋና የአብነት ትምህርት ላለፉት ዘመናት በአገረ መንግስት ግንባታ የነበራቸው ሚና እንዲሁም ያነበሩት አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ አዘጋጆቹ ባዘጋጁት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲናገሩ አድምጠናል።


ማኅበረ ቁስቋም ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በሰሜኑ እና በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤት ዙሪያ በርካታ ሥራዎችን ለመሥራት እቅድ ማቀዱ  በመግለጫው ተነስቷል፡፡ 


ፕሮጀክቱ “በእንተ ስማ ለማርያም ለእኔ ተማሪ” በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ከመጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የዘመቻ ሥራዎቹን እንደሚጀምር የሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።


ማኅበረ ቁስቋም፣ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በሰሜኑ እና በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤት ዙሪያ በርካታ ሥራዎችን ለመሥራት እቅድ ማቀዱ በመግለጫው ተነስቷል፡፡ 


ለዚህም “በእንተ ስማ ለማርያም ለእኔ ተማሪ” በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ከመጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የዘመቻ ሥራዎቹን እንደሚጀምር የሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።


በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ማኅበሩ የቤተክርስቲያኗን ቀኖና በጠበቀ መልኩ በሀገራዊ ጥናት እና ምርምር የሚዘጋጅ ዶክመንተሪ ለማቅረብ ውጥን እንዳለው ገልጿል ።


በሀያ የአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ ለሚገኙ ለ1ሺህ 200 የአብነት ተማሪዎች የሁለት ዓመት ቀለብ እና አልባሳት የማሰባሰብ እንዲሁም የሊቃውንት መምህራን ደምወዝ ክፍያ መፈጸም ላይ ማኅበሩ እንደሚሠራም አስታውቋል ፡፡


በዚሁ መሠረትም የአብነት ትምህርት የተማሪዎች ፣ የመምህራን ማረፊያ ፣ የመማሪያ ጉባኤ ቤት፣ የምግብ ማብሰያ፣ የተሟላ ቤተ-መጽሐፍት፣ የማምረቻ ሼድ ግንባታ ከሙያዊ ሥልጠና ጋር መገንባት መታቀዱን ከማህበሩ መግለጫ ተረድተናል ።


በሀያ የአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ ለሚገኙ ለ1ሺህ 200 የአብነት ተማሪዎች የሁለት ዓመት ቀለብ እና አልባሳት የማሰባሰብ እንዲሁም የሊቃውንት መምህራን ደምወዝ ክፍያ መፈጸም ላይ ማኅበሩ እንደሚሠራም አስታውቋል ፡፡


ማህበሩ በአብነት ትምህርት ቤቶች አስከፊ የኾነውን ተላላፊ በሽታ ታሳቢ በማድረግ የሙሉ ጤና ምርመራ የሙያ ፍቃድ ባላቸው ብቁ የጤና ባለሙያዎች ለማድረግ ማኅበሩ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን በመግለጫው ጠቅሷል። 


በተጨማሪም ማኅበረ የተለያዩ መንፈሳዊ እና ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ አውቀናል።


ለምሳሌም በሱስ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን በዕውቀት እና በክህሎት ማብቃት ይገኝበታል።


 የተዘጉ አቢያተ ክርስቲያናትን በማስከፈት፣ ገዳማትን መደገፍ፣ በሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ በኾኑ አደጋዎች ምክንያት በተለያዩ ችግሮቸ ውስጥ የሚገኙ ገዳማትን እና አድባራትን በማቋቋም ውጥን አለኝ ብሏል።


 (አማኑኤል ክንደያ)