መጋቢት 7 በሚሊኒየም አዳራሽ የመዝሙር ድግስ "ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ"

 ዜና




የዘማሪ ይድነቃቸው ተካ በሚሊንየም አዳራሽ መጋቢት  7 'ለት የመዝሙር ድግስ ሊያካሂድ መሆኑ ተሰማ።


የመዝሙር ድግሱ "ኢየሱስ ላዉድልህ ሀገሩን"  ይሰኛል።


ይህንን የሰማነው በስካይ ላይት ሆቴል የመዝሙር ድግሱን አስመልክቶ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።


በመግለጫው ዘማሪ ይድነቃቸው ተካን ጨምሮ የዝግጅቱ ተባባሪ አዘጋጆች በግንባር ቀርበው የመዝሙር ድግሱን አስመልክቶ ማብራራርያ ሰጥተዋል።


          photo : በስካይላይት ሆቴል መግለጫ ሲሰጡ


የዘማሪ ይድነቃቸው ተካ "ኢየሱስ ላዉድልህ ሀገሩን" የተሰኘ የመዝሙር ድግስ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት  7 ቀን 2016 ዓ.ም በሚኒሊየም አዳራሽ ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ይካሄዳል መባሉን ከመግለጫው መረዳት ችለናል ።


በተጨማሪም በመዝሙር ድግሱ ላይ ዘማሪው ያቀርባቸዋል ተብለው የሚጠበቁ መዝሙሮች ይድነቃቸው ተካ ቆየት ካሉትና ከቅርብ አመታት ወዲህ የተዘመሩ መዝሙሮች ናቸው ተብሏል።


ዝማሬዎቹ 16 መሆናቸውን ሰምተናል። 


በሚሊንየም አዳራሽ የሚካሄደው ይኸው  የመዝሙር ድግስ  የመግቢያ ክፍያ የሌለው መሆኑን አዘጋጆቹ ለመገናኛ ብዙሐን እወቁት ብለዋል።




ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ጀምሮ የሚሊኒየም አዳራሽ በሮች የሚከፍቱ ሲሆን ምዕምናን የመኪና ማቆሚያ መጨናነቅ እንዳይኖር አስቀድመው እንዲመጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ለማወቅ ችለናል ።


ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ በዝማሬው ዓለም ውስጥ በመቆየት እና በርካታ የዝማሬ ስራዎችን በመስራት እውቅና ያተረፈ ዘማሪ ነው፡፡ 


ይድነቃቸው ተካ፣ በአጠቃላይ ሁለት የመዝሙር አልበሞች በማቅረብ እና የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፀፆች በርካታ ተከታታዮች ያሉት ዘማሪ ነው።


የተለያዩ የመንፈሳዊ ስራዎቹን በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚያቀርብ  ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ ሲናገር ሰምተናል።


(አማኑኤል ክንደያ )