በሀገሬ ቴሌቪዥን የሚተላለፍ አዲስ ድራማ

 



ህሊና  ልብ አንጠልጣይ የሆነ የቴሌቪዥን ድራማ በኃይሌ ግራንድ ሆቴል የፊታችን ሐሙስ ሚያዚያ 3/2016  ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በርካታ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ተገኝተው መርቀውታል።


ሀገሬ ቴሌቪዥን ከሳልቃን ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር <<ህሊና >> ልብ አንጠልጣይ የሆነ የቴሌቪዥን ድራማ በኃይሌ ግራንድ ሆቴል የፊታችን ሐሙስ ሚያዚያ 3/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በርካታ የኪነጥበብ ባለሞያዎች፣ የሚዲያ ባለሞያዎች፣ የኮርፖሬት ተቋማት ኃላፊዎችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ተመርቋል ተብሏል።


"ህሊና" ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከተመረቀ በኃላ ከሚያዝያ 6 2016 ዓ.ም ዘወትር እሁድ ከ12:00 ጀምሮ በሀገሬ ቴሌቪዥን መተላለፍ ይጀምራል። 


የድራማው ዳይሬክተር በረከት ወረደ (ማያ) ሲሆን ደራሲ ዳንኤል ሰይድ ሲሆን ረ/ዳይሬክተር ዳዊት ፍስሃ ነው።




በተለያዩ ፊልሞች ላይ የምናውቃቸው እንግዳሰው ሀብቴ(ቴዲ) ፣ ቸርነት ፍቃዱ፣መሳይ ተፈራ፣ ፍናን ህደሩ፣ፈለቀ ካሣና ሌሎችም አንጋፋና ወጣት ባለሞያዎች በተዋናይነት ተሳትፈዋል።


ድራማው በአዲስአበባ እና ናዝሬት ከተማ የተቀረጸ ሲሆን በአጠቃላይ ከሁለት ዓመት በላይ የቀረጻ ጊዜ ፈጅቷል።


"ህሊና" ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በ19 ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ በጀት ወጥቶበታል።


የድራማው ምርቃት ሥነሥርዓት በሀገሬ ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ይሰጠዋል ተብሎአል።


(ንጋት ፕሬስ )