የሕንዱ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልኡካን ኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታልን ጉብኝት ማድረጋቸው ተገለፀ




የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ መልዕክተኛ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴዎስ ሣልሳዊ የተመራ ልኡክ የሆስፒታሉን የሕክምና አሰጣጥ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተመልክተናል ።

ሆስፒታሉ ከተከፈተ ጥቂት አመታት ቢሆኑትም እየሰጠው ያለው አገልግሎት በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሆስፒታሎች ተርታ መሰለፉ የሆስፒታሉ ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ተድላ ተናግረዋል።

አቶ ብርሃን ተድላ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ሆስፒታሉ ከሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ውጥን እንዳለው ገልፀዋል።

የጉብኝቱ ዋና አላማም ይኸው መሆኑን ጠቅሰው፣
በተለይ ከፍተኛ ሕክምናዎችን ወጪ የሚጠይቀው ዘርፍ በመሆኑ አገልግሎቱ በሀገር ውስጥ ለመስጠት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ለማሳስተዋወቅ ያለመ መሆኑን ሲናገሩ ሰምተናል።

 ሆስፒታሉ ዘመን አፈራሽ የቴክኖሎጂ መሳርያዎች የታገዘ መሆኑንና ይህንን ቴክኖሎጂ የሚያሳልጡ የሕክምና ባለሞያዎች አገልግሎቱን እየሰጠ መሆኑን ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ተድላ ገልፀዋል ።




በኢትዮጵያ ያለው የሕክምና አሰጣጥ ስርአት በርካታ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን ዘርፉ ካለበት ችግር ለማላቀቅ መዋእለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ የምጣኔ ሐብት አንቀሳቃሾች ይፈልጋል።

ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ይህንን ችግር ለመድፈን በብርቱ እየሰራ መሆን በተለያዩ የጤና ሚኒስቴር የስራ ሐላፊዎች በኩል በተደጋጋሚ ሲነገር መቆየቱን አይዘነጋም ።

ኢትዮጵያ የሕክምና ቱሪዝም በአገር ውስጥ ለመሳብ ጥረት እየተደረገ መሆኑንን ሲገለፅ የቆየ ሲሆን በመንግሥት ደረጃ እቅድ ተይዞ የተለያዩ እንቅስቃሴ እየተደረጉ መሆናቸውን የሚታወቅ ነው።

ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል የመንግስትን እቅድ እየተከተሉ ከሚገኙ ሆስፒታሎች መካከል ስሙ የሚጠቀስ ሲሆን፣ ከህፃናት እስከ አዋቂ በዘመናዊ መሳርያ የታገዘ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

በተጨማሪ የደረትና የሳንባ ቀዶ ጥገና ሕክምና ጨምሮ የጭንቅላትና ህብለሰረሰር ህክምና፣ የነርቭ ህክምና፣ የኩላሊት እጥበትና ህክምና፣ የአጥንት ቀዶ ሕክምና እና ጠቅላላ ህክምና እየሰጠ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ህንድ አራት ሆስፒታሎች ላይ በቦርድ አባልነት እና ሊቀመንበርነት እንደሚያገለግሉ ጠቅሰው፣ ኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ከእነዚህ ተቋማት ጋር አብሮ እንዲሰራ የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴዎስ ሣልሳዊ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ መልዕክተኛ በኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል እየሰጠ ያለበትን አገልግሎት ማድነቃቸውን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ሲናገሩ አድምጠናል።


በአማኑኤል ክንደያ