ቢዝነስ /ዜና
ቢክ እስኪብርቶ በኢትዮጵያ ማምረት ሊጀመር መሆኑን የተገለፀ ሲሆን አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተሰኘ ኩባንያ በኢትዮጵያ ማምረት ሊጀምር መሆኑን ተሰምቷል።
ኩባንያው ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ምርቱን ሲያከፋፍልና ወደ አገር ውክጥ ሲያስገባ መቆየቱን የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ላይ በአገር ውስጥ ለማምረት ከስምምነት ላይ መደረሱን ተነግሯል ።
ይህ የተነገረው የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስአበባ ስካይላይት ሆቴል በተደረገው የስምምነት ስነስርዓት ላይ ነው ።
አልሳም የተሰኘው አገር በቀል ኩባንያ ከሃያ አመታት በፊት ቢክ እስኪብርቶን በብቸኛ አስመጪነትና አከፋፋይነት ለአገር ውስጥ ለገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል ተብሏል ፡፡
ቢክ እሰሰክርቢቶ ከፍኛ ስም ያለውና እድሜ ጠገብ የሆነ ምርት ሲሆን በኢትዮጵያ ለረጅም አመታት በትምህርት አገልግሎት ሰጪ በመሆን ስሙ የተከለ ምርት መሆኑን ይታወቃል ።
ምርቱንም ከኬንያ አገር ሃኮ ኢንደስትሪስ በተባለው ተቋም ሲመረትና በአልሳም በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን አሁን ላይ በኢትዮጵያ መመረት እንደሚጀምር ተገልጧል ።
በአዲስአበባ በተደረሰው ስምምነት መሰረት አልሳም ከኢስት አፍሪካ ሊሚትድ ጋር በተደረገው የፊርማ ስነስርዓት ላይ መገለፁን ተረድተናል ።
ከዚህ በተጨማሪ የምርቱ ስርጭት ለምስራቅ አፍሪካ አገሮች ኢትዮጲያን ጨምሮ ለጅቡቲ፣ ለሶማሊያና ለኤርትራ የማከፋፈል ውጥን እንዳለው
አስታውቋል ።
አልሳም ቢክ እስኪብሮቶን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማምረት ዛሬ የካቲት 29/2017 ዓም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ከኢስት አፍሪካ ሊሚትድ ጋር የአጋርነት ስምምነት አድርጓል።
አልሳም ከማምረቱ በተጨማሪ የምርቱ ስርጭትም ለምስራቅ አፍሪካ አገሮች ኢትዮጲያን ጨምሮ ለጅቡቲ፣ ለሶማሊያና ለኤርትራ የሚያከፋፍል ይሆናል።
የቢክ እስክብርቶ በኢትዮጲያ መመረት በአከባቢው ካለው የገበያ ስፋት አንፃር የቴክኖሎጂ ሽግግር ከመፍጠር በተጨማሪም ፣ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛልና ለዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።
በቀጣይ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በትምህርት ስርአቱ ያሉ የአቅርቦት ችግሮች ይፈታል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ።
አልሳም ኃላ.የተ.የግል ማህበር ከተመሰረተ 25 ዓመታት ገደማ እድሜ ያለው ሲሆን በአስመጪነት፣ በላኪነት፣ በአገር ውስጥ ንግድ፣ በሪል እስቴትና በማኑፋክቸሪንግ የሥራ ዘርፎች ከሚታወቅባቸው መካከል ናቸው ።
በስምምነት ስነስርዓት ላይም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮምሽነር ዘለቀ ተመስገን ጨምሮ የኩባንያዎቹ ኃላፊዎች የተገኙበት መሆኑን ሰምተናል ።
አማኑኤል ክንደያ
#Advertisements