ፋሲካ ባዛር እና ኤክስፖ የፊታችን መጋቢት 30 ይከፈታል ተባለ

 ዜና/ቢዝነስ 



የፋሲካ ባዛርና ኤክስፖው በሚሊኒየም አዳራሽ ለሸማቾችና አምራቾች የሚገናኙበት መሆኑን ተነግሯል ።


 የፋሲካ ባዛር እና ኤክስፖ አዘጋጁ ባሮክ ኤቨንትስ ሲሆን ከመጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉ ቀናት ውስጥ ለሸማቹና አቅራቢዎች ይገናኙበታል ተብሏል ።


ዝግጅቱን አስመልክቶ አዘጋጁ ባሮክ ኤቨንትስ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ዘግበዋል።


 አዘጋጁ ባሮክ ኤቨንት እንደገለፀው የዘንድሮ የፋሲካ ባዛር እና ኤክስፖ ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍል በዓልን ምክንያት አድርጎ ከሚገጥመው የዋጋ ንረት  

በተመጣጣኝ ዋጋ የሚሸምቱበት ነው ብሏል።


በተጨማሪም ፣ አምራቹና ከአስመጪው የሚገበያይበት፣ አምራች ከሸማቹ ምርቶችን በብዛት 

የሚያገኙበት መሆኑን በመግለጫው ተጠቅሷል ።


በአሉን ምክንያት አድርገው ከሚነሱ የዋጋ ጭማሪዎች በተመጣጠነ ዋጋ የሚያገኙበትናዐ

ከፍተኛ የገበያ ሽያጭ በማግኘት ተጠቃሚ የሚሆንበት ነው ተብሏል።


በዝግጅቱም ላይ ከሚቀርቡት ምርቶች መካከል አልባሳት፣ የስጦታ እቃዎች፣ አቅራቢና አስመጪ፣ የምግብና መጠጥ ምርቶች መሆናቸውን ተገልጿል ።


 በተጨማሪም፣ የቤት ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች በአጠቃላይ ከበዓል ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ማንኛውም ግብዓቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብበት መሆኑን አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ ተጠቅሷል ።


 በዚህም ዝግጅት በቀን ከሰባት ሺህ እስከ አስር ሺህ ሸማቾች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡


 የተለያዩ ድምፃዊያን የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ፣ የተለያዩ የመዝናኛ የምግብ እና የመጠጥ ፕሮግራሞች የሚገኙበት ባዛር እና ኤክስፖ ነው፡፡ 


ይህ ባዛር እና ኤክስፖ የፊታችን መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ሚኒስትሮች፣ ባለሀብቶች በተገኙበት በይፋ የሚከፈት ይሆናል ተብሏል ፡፡