ዜና/ ቢዝነስ
በኤሮ አይረን ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የቤት ውስጥ የማስዋብ ጥበብ ወይንም ኢንተሬር ዲዛይን የስልጠና ማእከል መክፈቱን ተነግሯል።
የባለሞያ እጥረት እንዳለው የሚነገርለት ዘርፍ ሲሆን የቤት ውስጥ ዲዛይን ወይንም የኢንቴረር ዲዛይን ዘርፍ ለማሳደግ የበኩሉን እየተወጣ ያለ ድርጅት ሲሆን የስልጠና ማእከል መክፈቱን አስታውቋል ።
በኤሮ አይረን ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የኮንስትራክሽን የሥራ መስክን ለማዘመን የሚያግዝ የማሰልጠኛ ማዕከል ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በርካታ ባለሞያዎች ማፍራት ውጥን ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ለመገናኛ ብዙሐን እወቁልኝ ብሏል።
ድርጅቱ ይህንን ያለው መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስአበባ ቤስት ዌስትን ፕላስ ሆቴል የማእከሉ አገልግሎት አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
በኤሮ አይረን ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ የኮንስትራክሽንና የኢንቴረር ዲዛይን ሥራዎችን በሙያው መሰልጠን ለሚፈልጉ ሁሉ የማሰልጠኛ ማእከላቱ እንዲመዘገቡ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ጠይቋል ።
ማሰልጠኛ ማእከሉ "ሪቪዚት ኢንስቲቱሽን ኦፍ ዲዛይን" የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን በኮንስትራክሽን ዘርፍ መሰልጠን ለሚሹ ሁሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተናግሯል።
ድርጅቱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተሰማርቶ ለስምንት አመታት ያህል እየሰራ ያለ መሆኑንና በዘርፉ ያገኘው ልምድን ጨምሮ የኢንተሬር ዲዛይን ስልጠናዎችን መስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የኤሮ አይረን ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ፍሬዘር ሲናገሩ ተደምጠዋል ።
ዋና ስራ አስኪያጅ ፍሬዘር ተሾመ እንደገለፁት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የጠበቁ ስልጠናዎችና ለመስጠት ዝግጅቶች መደረጋቸውን ገልፀው ዘመን አፈራሽ የሆነ ዎርክሾፖችን የተሰናዱለት መሆኑን ተናግረዋል ።
ድርጅቱ በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ክህሎት ያላቸውን ባለሞያዎች የማፍራትና አላማ እንዳለው ጠቅሰው ማሰልጠኛ ማዕከሉ በዘርፉ የበኩሉን ለማበርከት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ሲናገሩ ሰምተናል ።
በኢትዮጵያ የኢንተሬር ዲዛይን ማሰልጠኛ ተቋማት እጥረት እንዳለ ተደጋግሞ ሲጠቀስ መቆየቱን ጉዳይ ቢሆንም በኤሮ አይረን ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ. ማኅበር ክፍተትን ለመድፈን የበኩሌ አድርጋለሁ ብሏል።
የኮንስትራክሽን ዘርፍ በርካታ የሰው ኃይል የሚጠይቅና የዝያው ልክ የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግር እንዳለበት ሲገለፅ ይሰማል።
ይሁንና የባለሞያ እጦት ለመቅረፍ የተለያዩ ማሰልጠኛ ማእከላት እንደሚያስፈልጉ ሲነገር ቢቆይም ዘርፍ ያሉበት ችግሮች መቅረፍ ሳይቻል ቆይቷል።
በኤሮ አይረን ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማኅበር የተሰኘው ይኸው ድርጅት የራሱ ወርክ ሾፖችና የግንባታ ሳይቶች አዘጋጅቶ በተግባር የተመሰረተ ስልጠናዎችን ለመስጠት መዘጋጀቱን ከመግለጫው መረዳት ችለናል ።
ማህበሩ የኮንስትራክሽንና የኢንቴረር ዲዛይን ሥራዎችን በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ በሙያው መሰልጠን ለሚፈልጉ ሁሉ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ ብሏል።
የክፍያ ሁኔታ አስመልክቶ የተመጣጠነና አካታች መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ክፍያቸዉን በፍጥነት መፈፀም ለማይችሉ ሰልጣኞች ከዳሽን ባንክ ጋር በመሆን ልዮ የብድር አገልግሎት እንደሚሰጥም ተናግረዋል።
የብድር ሁኔታው እስከ አንድ ዓመት የሚቆይ የብድር መክፈያ መንገድ መመቻቸቱን ገልፆ የተፈጠረው እድል በተለይም ወጣቶች እንዲጠቀሙበት ያለመ መሆኑን ተገልጿል ።
በአማኑኤል ክንደያ
Advertisements