ዞማ የውበት ማሰልጠኛ ማእከል በአዲስአበባ ተከፈተ

 ዜና/ፋሽን




ዞማ የውበት አጠባበቅ ማሰልጠኛ ማእከል ከዚህ ቀደም ዞማ ሰው ሰራሽ ፀጉር  (ሂዩማን ሄር) ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ከፍተኛ ስም ያተረፈው ድርጅት ሲሆን አሁን ላይ በመሐል ቦሌ ርያሊቲ ፕላዛ  ማስልጠኛ ማእከል ከፍቷል።


ዞማ የውበት አጠባበቅ ማሰልጠኛ ማእከል የተለያዩ የኪነ ውበት አጠባበቅ ስልት ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን ማእከሉ በውጭ አገራት ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች ትምህቱ የሚሰጥ መሆኑን ተገልጿል።


ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ዞማ ሄር በሚል የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ላይ ድርጅቱን በማስፋፋት የማሰልጠኛ ማእከል መክፈቱንና የተቋሙን አድማስ እያሰፋ መምጣቱን የድርጅቱ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ አርአያ ሐጎስ ተናግረዋል ።


የውበት ማሰልጠኛ ማእከሉን በማስተዋወቅ ረገድ አርቲስት ሊድያና ሰለሞን የድርጅቱ አምባሳደር በመሆን ተቋሙን እንድታስተዋውቅ መመረጧን ከተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መረዳት ችለናል።




ዞማ የውበት መጠበቅያ ማሰልጠኛ ማእከል ዘመን አፈራሽ መሳርያዎች ያሉት ሲሆን በአጠቃላይ የማእከሉ አቀማመጥ ለአይን በሚማርኩ ቴክኖሎጂዎች ያሸበረቀ መሆኑን ተመልክተናል ።


ተቋሙ የሚያሰለጥናቸው ሰልጣኞች በሞያ ብቻም ሳይሆን የስራ ዲስፕሊን የተቀረፁ እንዲሆኑ በማስቻል ረገድ እንደሚሰራ የተገለፀ ሲሆን አስልጣኞቹ ከፍተኛ የስራ ልምድ ያላቸው መሆናቸውን የድርጅቱ ባለቤትና ስራአስኪያጅ አርአያ ሐጎስ ገልፀዋል ።


አርአያ ሐጎስ በመግለጫቸው፣ የአሰልጣኞቹ የስራ ዘመን አገስተኛው አስራ አምስት አመታት ሲሆን ከፍተኛው ሐያ አምስት አመታት የስራ ልምድ ያላቸው መሆናቸውንም አስታውሰዋል ።




 


አሁን ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣው የስነ ውበት ጥበብ ዞማ የውበት ማሰልጠኛ ማእከል የበኩሉን ድርሻ ለማበርከት እንደሚሰራም የድርጅቱ ባለቤት ስራ አስኪያጅ  አርአያ ሐጎስ ከሰጡት መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።


የስልጠና ማእከሉ እውቅና ባገኘንባቸው የሜካፕ፣ የፌሻል፣ የጥፍር እና የፀጉር ስራ እንዲሁም የአይላሽ እና የኦምብሬየ የሙያ ዘርፎች ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ነው የተነገረው።


የተገለፀ ሲሆን የድርጅቱን አላማና የስራ ክንውን ወደ ህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ የማርኬቲንግና የማስታወቂያ ባለሙያ ሞዴል ሊዲያና ሰለሞንን የድርጅቱ አምባሳደር አድርጎ ሾሟታል፡፡ 


አርቲስት ሊዲያና ባላት ጠንካራ የስራ ባህል፤ በመልካም ስነ ምግባርና፣በከፍተኛ  ጥረት እራሷን  ለስኬትበማብቃት ለሴቶችና ወጣቶች መልካም አርአያ በመሆኗ ድርጅቱ ጋር እንድትሰራ መወሰኑን ተነግሯል ።


የሙያ ስልጠናዎችን ከመስጠት ባሻገር በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎትና ራእይ ላላቸው በፋይናንስ ችግር እጅ ላጠራቸውና  መማር ያልቻሉ ሰልጣኞችን ለማገዝ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመነጋገር በአነስተኛ ቅድመ ክፍያ የዱቤ አገልግሎት አግኝተው የሚማሩበትን እድል አመቻችቷል፡፡ 


እድሉን ዃንተም ቴክኖሎጂስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር ከተሰኘ ተቋም ጋር በመተባበር የብድር አገልግሎት ማመቻቸቱን ሰምተናል ።


በአማኑኤል ክንደያ


                        ADVERTISEMENTS