የነዳጅ ላኪ አገሮች ድርጅት የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋን መቀነስ የሚያስችል ርምጃ ወሰደ

 ዜና/ምጣኔ ሐብት 




የነዳጅ ላኪ አገሮች ድርጅት በምሕፃሩ ኦፔክ አባል ሀገራቱ የድፍድፍ ነዳጅ ምርት ዋጋን መቀነስ የሚያስችል ርምጃ መውሰዳቸውን ተሰምቷል ።


ስምንት  የኦፔክ ሀገራት  የድፍድፍ ዘይት ምርትን በቀን በ411 ሺህ በርሜል አሳድገዋል። ርምጃው የድፍድፍ ዘይት ዋጋን በስድስት በመቶ ይቀንሳል ተብሎለታል።


ስምንት የኦፔክ ዘይት አምራች ሀገራት ከግንቦት ወር ጀምሮ የድፍድፍ ዘይት ምርትን ለማሳደግ ተስማምተዋል።


ኦፔክ ባወጣው መግለጫ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሩሲያ፣ ኢራቅ፣ ኤምሬትስ፣ ኩዌት፣ ካዛኪስታን፣ አልጄሪያ እና ኦማን ምርቱን በቀን ከሚጠበቀው በላይ ወደ 411 ሺህ በርሜል ለማሳደግ ማቀዳቸውን አሳውቀዋል።




በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የምርት ማስተካከያ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል።


ቡድኑ የነዳጅ ዘይት ገበያ መረጋጋትን መደገፉን እንደሚቀጥልም የኦፔክ አባል ሀገራቱ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።


ርምጃው በለንደን ግብይት በበርሚል 70 ነጥብ 50 ዶላር የነበረው ለአይስ ብሬንት የነዳጅ ዋጋ በ5 ነጥብ 94 በመቶ ዝቅ እንዲል አደርገዋል።


የኦፔክ ሀገራት ከዚህ በፊት በቀን ከሚያመርቱት በቀን ከ140 ሺህ በርሜል በታች ምርት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ገበያው ላይ ከፍተኛ ለውጥ የሚያሳይ መሆኑ ተነግሯል ።