ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ሚድያ የተሰኘ የቤት ቁሳቁስ አቅራቢ ድርጅት የብራንድ አምባሳደርነት የስራ ውል ስምምነት ማሰሯ ተሰምቷል ።
ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ ለሚድያ ድርጅት ለቴሌቪዥን፤ቢል ቦርድ እና ለማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎች ለመስራት መስማቷን ተገልጿል፡፡
ስምምነቱ ለሁለት አመታት የሚቆይ ሲሆን ድምፃዊቷ የአምባሳደርነት ስምምነት ከድርጅቱ ጋር ለመስራት መመረጧ እንዳስደሰታት በአዲስአበባ በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል ።
ሚድያ በ1968 በቻይና ውስጥ የተመሰረተና ኢትዮጵያ ጨምሮ 200 በላይ ለሚሆኑ ሀገሮች ምርቶቹን እንደሚልክ የተገለፀ ሲሆን በአለምአቀፍ ደረጃ ደግሞ ግንባር ቀደም የቤት እቃ አምራች ድርጅት መሆኑ ተገልጿል።
ስምምነቱ ሚድያ ከድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ጋር የተለያዩ ማህበራዊ ግዴታዎቻችንን ለመወጣት እና ህዝቡ ጋር የነበረውን ተደራሽነት በተሻለ መልኩ ለማጎልበት የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት መሆኑን በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ተነግሯል።
እንዲሁም ተወዳጅዋ ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ በሚድያ ለቴሌቪዥን፤ቢል ቦርድ እና ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎች ለመስራት ተፈራርማለች፡፡
ሚድያ ከድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ጋር የተለያዩ ማህበራዊ ግዴታዎቻችንን ለመወጣት እና ህዝቡ ጋር የነበረውን ተደራሽነት በተሻለ መልኩ ለማጎልበት የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ስምምነቱን እንዳረገ ተነግሯል።
አርቲስቷ የተመረጠችበት ምክንያቶችም ማህበራዊ ግዴታዎቿን በተቻላት መጠን የምትወጣ ክብሯን ጠብቃ ስራዋ ላይ ብቻ የምታተኩርና ማንም ላይ የማትደርስ ትክክለኛ ኢትዮጵያት ሴት ስለሆነች ነው ተብሏል።
ሚድያ በ 1968 በቻይና ውስጥ የተመሰረተ ሲሆን ከ 200 በላይ ለሚሆኑ ሀገሮች ምርቶቹን ይልካል ከአለም ደግሞ አንደኛ የቤት እቃ አምራች ድርጅት ነው።
በኢትዮጲያ የሚድያን ምርቶች ከ2018 ጀምሮ በብቸኝነት ማስመጣት የጀመረ ሲሆን ቬሮኒካ አዳነ የብራንድ አምባሳደር ሆና ተመርጣለች መባሉን ሰምተናል ።
ሚድያ የቁሳቁስ አምራች ድርጅት መሰረቱ ቻይና ሲሆን የእንግሊዝ ክለብ ማንቸስተር ሲቲ የድርጅቱ ማስታወቂያ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያለውን የማስታወቂያ ስራ ቬሮኒካ አዳነ ትሸፍነዋለች ተብሏል።
ድርጅቱይ በማስተዋወቅ ረገድ ሐላፊነቷን በአግባቡ እንድትወጣ ሚድያ የቁሳቁስ አምራች ድርጅት በአደራ መስጠቱን በስካይ ላይት በነበረው መግለጫ መረዳት ችለናል።
አማኑኤል ክንደያ
ADVERTISEMENTS