የሰሚነሽ ኪ/ምህረት ገዳም አርብ 'ለት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ይጀመራል ተባለ

 ዜና




የአንጎለላ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት ገዳምን ለማስፋፋት መዋእለ ንዋይ እንደሚያስፈልግ ተነግሯል ።


የሰሚነሽ ኪዳነ ምሕረት ገዳምን ለማስፋፋት አማንያን የሚቻላቸውን እንዲያደርጉ ድጋፍ እየተጠየቀ መሆኑን የገዳሙ አባቶች ተናግረዋል ።


ገዳሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያስተናግዳቸው አማንያን እየጨመረ በምምጣቱ የተነሳ ገዳሙ ላይ ያሉ መሰረተ ልማቶች ለማስፋት ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ እንደጠየቃቸው የገዳሙ ሐላፊዎች ገልፀዋል።


ገዳሙን ለማስፋፋት የተወጠነው ውጥን ዳር እንዲደርስም ምእመናን የበኩላቸውን አስተደዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥያቄ መቅረቡን የገዳሟ ሐላፊዎችና የሀይማኖት አባቶች በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል ።


አክለውም ፣ በጅምር ከቀሩ ሥራዎች መኖራቸውን ጠቅሰው የተነሱ የመቃብር ቦታዎች  መኖራቸውንና ለዝያ ምትክ ዘላቂ ማረፊያ ወይም ፉካ መስራት በማስፈለጉ በኮንክሪት የሚሠራ ፉካ ለማዘጋጀት ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ ፕሮጀክት መያዙን አንስተዋል ።




የገዳሙን ቅፅር ግቢውን ለማስፋፋት ከቦታው ለተነሱ የግለሰቦች መኖሪያ ሥፍራዎች ምትክ ቦታ እና የካሣ ግምት ክፍያ ከገዳሟ አቅም በላይ መጠየቃቸውንና ለዚህም እገዛ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ።


ከዚህ በተጨማሪም፣ ወደ ገዳሟ የሚመጡ ምዕመናን ቁጥር በእጅጉን እየጨመረ መምጣቱን የተነሳም ተጨማሪ 45000 ሰው ማስተናገድ የሚችል አዳራሽ በማስፈለጉ ለማስገንባት ውጥን መያዙን ከሐላፊዎቹ መግለጫ መረዳት ችለናል ።


ይህ እንዲህ እንዳለም፣ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ  ባለ ሶስት ደብር ህንፃ ሥራ በጅምር ላይ መሆኑንና ፣ 14 ሰንበቴ ቤቶችን ግንባታ በስራ ላይ መሆኑን አንስተዋል ።


ገዳሙ ፣ ለጽኑ ሕሙማን ማረፊያ ፣ መንከባከቢያና ለዊልቸር መተላለፊያ የተዘጋጀለት ሕንጻ ለመገንባት ፣ የኦቲዝም በሽታ ተጠቂ ለሆኑ ህጻነትና ምዕመናን ለብቻ ማረፊያ የተለየ ቦታ ለመስራት እቅድ እንዳለው ገልጿል።


በአጠቃላይ በዝርዝር የተቀመጡ ተግባራትን ለማከናወንና ልማት ሥራዎቹ ለማከናወን ሕዝበ ክርስቲያን የበኩሉን እንዲያደርግ ተጠይቋል።


መግለጫው የተሰጠው በአዲስአበባ አዜማን ሆቴል ሲሆን በተለያዩ ንግድ ባንኮች በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ የሚቻል መሆኑን ከገዳሙ ሐላፊዎች ሰምተናል ።

 በአማኑኤል ክንደያ