የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት በአስር አመታት ውስጥ ገንዘብ ሽሽት በታሪክ ታይቶ አያውቅም

 





አጭር ቆይታ- ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ


ፕሮፌሰር አለማየሁ በቅርቡ የደረሱበት አንድ ጥናት አለ።

ኢትዮጵያ በ10 ዓመት ውስጥ ከሀገር የሸሸባት ሀብት ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ይገመታል ።

የምጣኔ ሀብት ተመራማሪው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ በኢትዮጵያ በ10 ዓመት ውስጥ ብቻ 45 ቢሊየን ዶላር ከሀገር መውጣቱን ገልጸው ይህም የ10 ዓመቱን ወደ ውጪ የሸሸ ኃብት ከባለፈው 44 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ዓመቱ እንደሚበልጥ ተነግረዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪው በ44 ዓመት ውስጥ ከኢትዮጵያ የሸሸው ሀብት 31 ቢሊየን ዶላር ነው።  ይህም በጥናት ተረጋግጦ መታተሙን ፕሮፌሰሩ አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በከተማው ውስጥ ከመደበኛው ሥርዓት ውጪም ከፍተኛ ዶላር እንደሚገላበጥ ያስረዳሉ።


- ለመሆኑ ዋናው ምክንያት ምንድነው?


ለዚህ የዶላርና የገንዘብ ፍልሰት (Capital Flight) ዋነኛው ገፊ ምክንያት በሀገር ውስጥ ያለው የደኅንነት ስሜት አለመኖር እና መንግስት በብርቱ ባለመቆጣጠሩ ነው ብለዋል።


- ስለዚህ ምን መሰራት አለበት?


በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር አሁንም እንዳይሸሽ መንግስት ቀዳዳዎችን እየደፈነ ከፖሊሲ ባልተናነሰ ችግሮችን እየለየ መሰራት እንዳለበት ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የዶላር ግብይት ሥርዓት ላይ መሰረት የማዕድን አካባቢዎችና የኬላ ቁጥጥር ላይ መስራት በአጠቃላይ ህግና ሥርዓት ላይ መስራት "ከኤክስፖርት የማይተናነስ [ገቢ] ሊያመጣልህ ይችላል።" ብለዋል።


- የዶላር ገበያን ነጻ ማድረግ አማራጭ ነው?


ፕሮፌሰር አለማየው ገዳ ኢትዬጵያ እየተከተለችው ያለውን የህገ ወጥ ዶላር ቁጥጥር  "አጭበርባሪ ፖሊሲ" ሲሉ ይገልፁታል። "የህገወጡ ገበያ ሁልጊዜ እንደ ጥላ ነው። ስትሄድበት ይሸሻሀል። ያለፉት አራት አመታት ያየነው ይኸው ነው። ምን መረጃ ያስፈልጋል አየነው እኮ ላለፉት 4 ዓመታት፤ እንደው ጥናትም ሪሰርችም አያስፈልግም! ... እዚያ ያለው ገቢያ በተፈጥሮው በህጋዊው ገቢያ አይስተናገድም [አንዳንዱ] ህጋዊውን ብጨምረው ያም ተመልሶ ይጨምራል" ሲሉ ያስረዳሉ።