ንጋት - ከጥበብ ገጽ
[ ማስታወሻ ]
🎼 ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ
ይኽ ሰው የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት መስራች እና ዝነኛ አቀናባሪ ነው ።
ፕሮፌሰር አሸናፊ በሙዚቃ አቀናባሪነቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊገዳደረው የሚችለው ሙላቱ አስታጥቄ ብቻ እንደሆነ ይነገራል ።
"እረኛው ባለዋሽንቱ" (The Shepherd flutist) በሚባል ቅንብሩ ይታወቃል።
ይኽንን ሙዚቃ ግርማ ይፍራሸዋ እና ሌላ አንድ የሃንጋሪ ኦርኬስትራ ሙዚቀኛ ተጫውቶታል ።
ጥቁሩ ኮዳሊ በመባልም ይታወቃል ። ኮዳሊ ዝነኛ የሃንጋሪ ሙዚቃ አቀናባሪ ነው ።
ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ በ1963 እ.ኤ.አ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤትን መስርቷል ።
1967 እ.ኤ.አ የሀገሪቱ ብሔራዊ ሙዚቃ አቀናባሪ ተብሎ የሃይለስላሴን ሽልማት አሸንፏል ።
ልጁ ሰናይት አሸናፊ በሆሊውድ የፊልም ተዋናይት ናት ።
ፕሮፌሰር አሸናፊ በ60 አመታቸው በልደታቸውን ቀን በቤቱ ነበርሞቶ የተገኘው ።
አሸናፊ የራሱን ህይወት ታሪክ እንደጻፉ ይገመታል፤ ምክንያቱም በጥልቅ ተመስጦ አብሮሆት/Nirvana ላይ ስለደረሰ ከዚህ በላይ መኖር ትርጉም አልባ ሆኖ እንዳገኘው ለጓደኞቹ በጽሕፈው ያስቀመጠው ደብዳቤ ይመሰክራል ።
