የምጣኔ ኃብት ዝግጅት

 





ሮበርት ሶሎው የምጣኔ ሀብት ሞዴል 


ስለ ማክሮ ኢኮኖሚ ወሳኝ ነጥቦችን ለማንሳት ብንሞክር በመጀመሪያ ረድፍ የምናገኘው የኢኮኖሚ እድገት መሰረታዊ ምክንያቶች በሞዴል ያስቀመጠው በኢኮኖሚክስ 1987 የኖቤል ሽልማት ያገኘውን እና በስሙ የተሰየመለትን Solow Growth Model የፈጠረው" ሮበርት ሶሎው " ዋናው ነው።


 ሮበርት ሶሎው 1960ዎቹ በጻፈው “A Contribution to the Theory of Economic Growth’’ ቁጠባ፤ የህዝብ ቁጥር ብዛት እና እድገት እንዲሁም የቴክኖሎጂ መዘመን እንዴት የአንድ ሀገርን የኢኮኖሚ ጠቅላላ ምርት እና ቀጣይነት ያለው እድገትን ተጽኖ እንደሚያደርግ አስረድቷል።


ሶሎው ሀብት ሞዴል የካፒታል ክምችት (Capital stock)፣ ለስራ ዝግጁ የሆነ የሰው ሃይል መብዛት (Growth in the labor force) እና የዘመነ ቴክኖሎጂ መኖር በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖረውን ጠቅላላ የምርት እና የአገልግሎት አቅርቦት ተጽኖ እንደሚያደርግበት በግልጽ አስረድቶ ነበርም።


ለምሳሌ ለአንድ አገልግሎትም ሆነ ምርት በገበያ ላይ ስለሚኖረው አቅርቦትም ሆነ ፍላጎት ለማምረት በግብዓትነት የሚያስፈልገው በቂ ካፒታል (Accumulation of capital) መሟላት አለበት (ፋብሪካ እንዲያመርት ማሽነሪ እና ህንጻው እንደሚያስፈልገው ማለት ነው) ነገር ግን ለውድድር እንዲያገለግል የሰው ሃይል እና የቴክኖሎጂ ተጽኖ ካፒታልን በምናወዳድርበት ወቅት አይለዋወጥም። "We assume that the labor force and technology are fixed" ይለዋል።


ሶሎው ሞዴል በሀገራቶች መካከል ያለው የዜጎች የገቢ መጠንም ሆነ አጠቃላይ በሀገሪቷ ውስጥ ያለው የጠቅላላ የምርት መጠን (Economy’s output) የሚለያይበት ዋናው ምክንያት ከሌሎች ሀገራቶች በተለየ መልኩ ያላቸው የካፒታል ክምችት (መሰረተ ልማት ልንለው እንችላለን)፣ ለስራ ዝግጁ የሆነ የሰው ሃይል መብዛት እና የዘመነ ቴክኖሎጂ መኖር ነው ብሎ ያምናል።


መሰረተ ልማት ለኢኮኖሚ አጠቃላይ ምርትም ሆነ አገልግሎት ወሳኝ ግብዓት ቢሆንም፤ ነገር ግን በ Investment እና Depreciation ተጽኖ ውስጥ ነው። ምክንያቱም መሰረተ ልማት ለማሟላት ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል። ለምሳሌ ምርት ለመጀመር አዳዲስ ፋብሪካ መስራት፤ አዳዲስ ማሽነሪዎች ለመግዛት ገንዘብ ያስፈልጋል ይሄ ደግሞ Capital stockን ሲያሳድግ በሌላ መልኩ ደግሞ መሰረተ ልማት ከተሰራ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች Depreciation በማድረግ የአገልግሎት አቅማቸውን ስለሚያጡ  ለተጨማሪ ወጪ ይዳረጋሉ ማለት ነው ይለዋል።


 በዚህ ምክንያት Capital stock ይቀንሳል።


ሶሎ የሀብት ሞዴል በግራፍ በማስደገፍ ብዙ ሃሳቦችን በማስረጃ የሚያስረዳ ድንቅ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ቲዎሪ ነው።


  ( “A Contribution to the Theory of Economic Growth,’’  ከተሰኘው መፅሀፉ የተወሰደ )