- ኪይ ሀውሲንግ የፋይናንስ ሶሊሺን የተባለ በቤት ልማት ላይ የተሰማራ ኩባንያ መካከለኛ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት የሚያገኙበትን የቤት ልማት መጀመሩን ተናገረ።
ኩባንያው በአስር አመታት ውሰጥ ለአንድ መቶ ሺ የቤት ጠቃሚ ህብረተሰቦችን ገንብጦ በእጣ መልኩ እንደሚያከፋፍል ዛሬ በአዲስ አበባ በሀያት ሪጄንሲ ሆቴል ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።
ኩባንያውየእጣ አወጣጡ አስመልክቶ በሰጠው ማብራሪያ በአመት ሁለት በየ ስድስት ወሩ ለባለ እድለኞች የእንደሚያወጣ ገልፆ ፣ በቀጣይ አስር አመታት ውስጥም ሀያ ጊዜ እንደሚያከናውን ነው።
የተጠቃሚዎች የገንዘብ ዋስትና በተመለከተም ዳሽን ባንክ በዝግ አካውንት የሚያስተዳድረው ሲኾን፣ ቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ ደግሞ የመድህን አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
ደንበኞች የሚቆጥቡበት የቁጠባ ሞዴል KCHF ይሰኛል።
ባለ አንድ ከፍሉ ቤት ከ40 ካሬ ሜትር ሲጀምር ሁለት እና ሶስት ክፍሎች ደግሞ ከ 70 እና 120 ካሬ ሜትር ይጀምራሉ ሲል የኩባንያው ማቀብራርያ ሲሰጥ ተሰማምቷል ።
የብድር ሞዴሉ ለመመዝገብ 77,280 ብር የሚከፈል ሲሆን ለአምስት አመት ኢንሹራንስ 2,672 ብር የሚከፈል ይሆናል።
ባለ አንድ ክፍል ዕቁብኞች ዕቁቡ እስኪደርሳቸው ድረስ ወርሃዊ መዋጮ 2,230 ብር የሚከፍሉ ሲሆን ባለ ሁለት እና ሶስት ክፍል ዕቁብተኞች 2,730 እና 3,730 ብር በየወሩ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
ዕጣ ሲወጣላቸው ደግሞ ባለ አንድ ክፍል ዕቁብተኞች 300,000 ብር የሚከፍሉ ሲሆን ባለ ሁለት እና ሶስት ክፍል ዕቁብተኞች 550,000 እና 800,000 ብር ይከፍላሉ ተብሏል።
ሁሉም ዕቁበተኞች ቤት ከተገዘላቸው በኋላ በወቅቱ በሚተመን የቤት ኪራይ ወርሃዊ ዋጋ ለአምስት አመት ለኪይ ሲኤች ኤፍ የቤት ኪራዩን የሚከፍሉ ሲሆን ይሄን ካልፈለጉ ለሌላ ሰው ቤቱን በእራሳቸው ዋጋ አከራይተው የሚጠበቅባቸውን ኪራይ መክፈል ግን ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
(ንጋት ፕሬስ)
