ያልተዘመረላቸው የእፅዋት ሊቅ ፕሮፌሰር ለገሰ ነጋሽ


 ያልተዘመረላቸው የእፅዋት ሊቅ ፕሮፌሰር ለገሰ ነጋሽ



 ~ ማስታወሻ 

በአለም የእፅዋት ምርምር ዘርፍ በጣም የተከበሩ ኢምሬትስ ፕሮፌሰር ለገሰ ነጋሽ  ናቸው።

እነኚህ ሽልማቶች ከሳሎን ተቀምጠን ስንጨዋወት ከተቀመጥኩበት ያነሳሁት ፎቶ ነው።

ፕሮፌሰሩ ጋር ለአንድ ቀን ከቤታቸው አብረን ዋልን።  ምሳ፣ ሻይ ፣ እውቀት፣ ልምድ፣ ራእይ፣ ተፈጥሮ፣ ህልም፣ ሰነፅሁፍ ያልኮመኮምኩት ነገር የለም ማለት ይቻላል።

ፕሮፍ. ለገሰ ነጋሽ አርባ አመታት በአገር በቀል እፅዋት ምርምር ብቻ አሳልፈዋል ። እንዴት ያለ እውቀት እንዳላቸው አንባቢዎች እስኪ ገምቱት። በሌላው አለም በጣም የታወቁ ናቸው ፤ በተለይ በሳይንስና አካዳሚው አለም " ኢምሬትስ ፕሮፌሰር " ናቸው።

በአገር ቤት ግን የሚያውቋቸው ጥቂቶች ናቸው።

በኢትዮጵያ ለሞያቸው ተገዝተው ለአገራቸው ከልብ የደከሙ ተመራማሪዎች ከአስር አይበልጡም፤  ከነዝያም የፊተኛው ረድፍ የሚይዙት( ፕሮፌሰር ) ባህሩ ዘውዴ ፣ ለገሰ ነጋሽ፣ ባዬ ፣ መሰፍን ወ/ማርያም፣ አሸናፊ ከበደ ናቸው።


 ሌላው አይመስለኝም፤ ከይቅርታ ጋር ...


የአገር በቀል እፅዋት መመራመር፣ ማወቅ፣ ማሰስ ምንኛ ደስ ያሰኛል እኝህ ለገሰን ቀርቦ ላወቃቸው ሰው።

በህይወቴ እንዲህ ያለ ጥልቅ እውቀት ያለው ሰው ገጥሞኝ አያውቅም።

ሰውየውን ለሰባት ሰአታት ያህል ያለማቋረጥ ቤታቸው ተገኝቼ በመቅረጫዬ ቀድቻለሁ። 

በሞያዬ ረጅሙ ቃለ መጠየቅ ነው ማለት ይቻላል።


ተዝቆ የማያልቅ እውቀት ።

 

በኢትዬጽያ ፈር ቀዳጅ የአገር በቀል እፅዋት ተመራማሪ ኢምሬትስ ፕሮፌሰር ለገሰ ነጋሽ በአለማቀፍ ጆርናሎች አየር ንብረት ለውጥ ዙርያና የኢትዬጵያ አገር በቀል እፅዋቶችን የሚያትቱ ፅሁፎች አሳትመዋል። 

 ኢምሬትስ ፕሮፌሰር ለገሰ ነጋሽ ለአለምና ለሰው ልጆች ህይወት ለማትረፍ ላበረከቱት አስተዋፅኦ በሚል በርካታ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል።