ኢትዮጵያ "የብሪክስ አባል" መሆንዋ የአለማቀፍ መገናኛ ብዙሐን እየዘገቡ ነው።
የአለም የኢኮነሚ አሰላለፍ እየተቀየረ መምጣቱን ብዙ ማሳያዎች እየታየ በመሆኑ ኢትዮጵያ ከብሪክስ ጎን መሆን እሻለሁ ስትል ውሳኔ አሳልፋ ነበር።
በዚሁ መሰረት ለብሪክስ አባል አገራት ማህበሩን ለመቀላቀል በቅርቡ ያስገባችው የመጠየቅያ ደብዳቤ መሠረት በደቡብአ ፍሪካ ጁሀንስበርግ ከተማ በተደረገው 15 መደበኛው በጠቅላላ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በተሳተፉበት ስብሰባ ለሥስት ቀናት ሲካሄድ ሰንብቶ ነበር ።
የብሪክስ አባል አገራቱ ይህን ውሳኔ ለማፅደቅ ጠረጴዛ ተቀምጠው ባደረጉት ምክክርና የውስጥ ጉባኤ ኢትዮጵያ የብሪክስ ማህበርተኛ እንድትሆን ይሁንታ ውሳኔ አሳልፏል
በደቡብ አፍሪካዋ ጁሃንስበርግ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 15ኛው የብሪክስ አገራት የመሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት አገራት የብሪክስ አባላት እንዲሆኑ ተቀባይነትን አግኝተዋል፡፡
አገራቱ ኢትዮጵያ፣ አርጀንቲና፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መሆናቸውን፤ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አስታውቀዋል፡፡
ብሪክስ በመባል የሚታወቀዉ የአምስት ሃገራት ሥብሥብ ማህበር ነው።
የብሪክስ አባል አገራት ብራዚል፣ ሩስያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃ ከዓለም ኢኮኖሚ አንድ አራተኛውን የሚያንቀሳቅሱ ሀገራት ናቸው።
እንደሚባለው ብሪክስ ፣ የአውሮፓ እና የዩናይትድ ስቴትስን ግዙፍ ተፅዕኖ ለመቋቋም እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን በመንቀሳቀስ ላይ ያለ ማህበር ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ጥቂት የማይባሉ ሀገራት የብሪክስ አባል ለመሆን እየጠየቁ ነው።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ሳውዲ አረቢያ፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ኢራን፣ ቱርክ፣ ግብጽ እና አልጀሪያ የአባልነት ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት መካከል ናቸው።
ከብሪክስ አባላት መካከል ጠንካራ የምጣኔ ሀብት የምታንቀሳቅስው ቻይና ማህበሩ እንዲስፋፋ በእጅጉ ትሻለች።
