በትራፊክ አደጋ ~ የፈጠራ ኃሳብ
ኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ አገራት ውስጥ በትራፊክ አደጋ በርካታ ህይወት የሚቀጠፍባቸው አገራት ግንባር ቀዳሚ ነች። በትራፊክ አደጋ ሳቢያ በርካታ ንብረትና ህይወት ተቀጥፏል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ አገራት በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሰዎች ህይወት ከሚቀጠፍባቸው አገራት 19ኛ ደረጃ ተመድባለች ። ይህም አደገኛ ከሚባልባቸው አገራት ተርታ ተሰልፋለች ።
በትራፊክ አደጋ የሚከሰት አደጋ ለማስቀረት ያለመ አንድ የፈጠራ ሀሳብ ተዋውቋል። የዚሁ የፈጠራ ሀሳብ ባለቤት ጎይቶኦም ገ/ ዮሃንስ ይባላሉ።
የትራፊክ አደጋ የሚከሰት ችግር ለመቅረፍ በርካታ አመታት ደክመዋል። ፈጠራ ሀሳቡ በአእምሮ ንብረት ባለስልጣን እውቅና የተሰጠው ሲኾን
በተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠም አውቶማቲክ አደጋ ጠቋሚ መሳርያ ነው። በተሽከርካሪዎች በቀኝ በኩል የሚገጠምና አሽከርካሪዎች ወደ ቀኝ ለመዞር፣ ለመታጠፍ በሚሹበት ጊዜ ምልክቱን በመጠቀም ከኃላ የሚመጣውን አሽከርካሪ በቀላሉ ተመልክቶ እንዲጠነቀቅ ይረዳዋል።
አሽከርካሪዎች ራሳቸውንና ህብረተሰቡን ከአደጋ እንዲጠብቁ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ታውቋል። አደጋ መከላክያው በተለያዩ የመኪና አይነቶች ውበት በማይነካና የአውቶሞቢሎችን ገፅታ በማያበላሽ መልኩ የሚገጠም ነው ተብሏል። ይህን የፈጠራ ሀሳብ በአገርቤት የሚገኙ የአውቶሞቲቭ መኪኖችን የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የፈጠራ ሀሳቡን እንዲጠቀሙበት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን የፈጠራ ሀሳቡ ባለ ቤት ጎይቶኦም ገ/ዮሃንስ ይናራሉ።
ይህ እንዲህ እንዳለ፣ የትራፊክ አደጋ መከላከያ ምልክት ከውጭ አገር የሚመጡት አውቶሞቢሎችና የተለያዩመኪኖች ላይ ሳይቀር ተገጥሞላቸው እንዲጠቀሙበት ይደረጋል ብለዋል የፈጠራ ባለቤቱ ጎይቶኦም።
ኢትዮጵያ ጀማሪ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ግለሰቦች በጣም ከሚቸገሩባቸው ፈተናዎች መካከል የፋይናንስ ድጋፍ ( start up ) ዋነኛው ጉዳይ ነው ።
የፈጠራ ባለቤቱ ጎይቶኦምገ/ዮሃንስ እንደሚሉት ከሆነ ግን የልማት ባንክ ባዘጋጀው ሀሳብን አስይዞ የሚገኘውን የፋይናንስ ድጋፍ ቋት (start up financing portal ) የፈጠራ ሀሳባቸውን አቅርበው ተቀባይነት ማግኘታቸውን ነው።
ይህንኑ የፈጠራ ሀሳብ ተግባራዊ እንዲሆንና በተሳለጠ መልኩ ግልጋሎት እንዲሰጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርንና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እንዲያደርጉ ይደረጋል መባሉን ከሀሳቡ ባለቤት ጎይቶኦም ገ/ዮሃንስ ሰምተናል።
የፈጠራ ሀሳቡ የፌደራል ፓሊስን ጨምሮ የትራፊክ ማነጅመንት ኤጀንሲ ፣ ትራንስፖርት ሚኒስቴርና የመንገድ ፈንድ ኤጀንሲ በትራፊክአደጋ የሚመጣ ችግር ስራቸውን በእጅጉ እንደሚያቀልላቸው ታምኖበታል።
በኢትዮጵያ እየደጋገማት ያለው በትራፊክ አደጋ የሚከሰት የዜጎች ህይወት ማጣትና በንብረት ላይ የሚደርስ አደጋ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል ።
ጎይቶኦም ገ/ዮሃንስ በሞያቸው በተለያዩ የመንግስትና የግል ድርጅቶች በቋሚነትና በጊዜያዊነት ተቀጥረው አገልግለዋል። ይህንኑ የፈጠራ ሀሳብ ሲያበለፅጉ ካላቸው መደበኛ ስራ በተጓዳኝነት ባደረጉት ከፍተኛ የምርምር መሆኑን ለንጋት ፕሬስ ተናግረዋል።
በቅርቡም የፈጠራ ባለቤቱ ሌላ ተጨማሪ የፈጠራ ሀሳቦች ይዘው እንደሚመጡ ይጠበቃል።
- በትራፊክ አደጋ የሚከሰቱ ችግሮች ቁጥሮች ምን ይናገራሉ ?
በኢትዮጵያ በየቀኑ በአማካይ 14 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ እና 31 ያህሉ ደግሞ ለከባድ የአካል ጉዳት እንደሚዳረጉ ከመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአገሪቱ ከሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች 68.3 በመቶ ያህሉ ምቹ በሆኑ መንገዶች ላይ የሚከሰቱ መሆናቸው እና ከሚደርሱት አደጋዎች መካከል 85.9 በመቶ በአሽከርካሪው ስህተት፣ 3.3 በመቶ በተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ጉድለት፣ 2.8 በመቶው ደግሞ በእግረኞች ችግር የሚያጋጥሙ ናቸው።
በመንገድ ችግር የሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች 0.7 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጥናት ያመለክታል፡፡
በኢትዮጵያ በ2014 ዓ.ም በትራፊክ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 3,971 ሲሆን፣ በ2013 ዓ.ም ከተከሰተው የሞት አደጋ ጋር ሲነጻጸር በ190 መቀነሱ ይነገራል።
በ5,911 ሰዎች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰ የመንገድ ደኅንነት እና የመድህን ፈንድ አገልግሎት አስታውቋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ2013 በጀት ዓመት ከ15 ሺህ በላይ የትራፊክ አደጋዎች ያጋጠሙ ሲሆን፣ በአደጋዎቹ ምክንያትም 4,161 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።