ከተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርስዎች የተውጣጡ መምህራን የተቋቋመው የግል ኮሌጅ

 





- ኤግል ኮሌጅ ለሁለተኛ ጊዜ በዲግሪ መርኃ ግብር ተማሪዎቹን አስመርቋል ።


ኤግል ኮሌጅ በዛሬው እለት 450 በዲግሪ ፕሮግራም ( በርቀት) ያስመረቃቸው ተማሪዎቹን በኦሮምያ ባህል ማእከል ማስመረቁ ታውቋል።


ኮሌጁ አካውንቲንግ ማኔጅመንት እንዲሁም በንግድ ሰራ ትምህርት ክፍሎች ለሁለተኛ ጊዜ ተቀብሎ ያስተማራቸው ተማሪዎች ማስመረቁ የንጋት ፕሬስ ዘጋቢ በምረቃ ስነስርዓቱ ከቦታው ዘግቧል።


ኤግል ኮሌጅ ከተለያዩ ዪኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ምሁራን በ2011ዓ.ም የተቋቋመ የግል ኮሌጅ የኮሌጁን ድህረ ታሪክ ይናገራል።


ኮሌጁን ያቋቋሙት ሙሁራን ከዚህ ቀደም ሲያስተምሩባቸው ከነበሩት ዩኒቨርስቲዎች ካገኙት ልምድ በመነሳት የምርምር ስራዎችን የሚያካሒዱበት የትምህርት ተቋም ነው።





በተለይም የትምህርት ስርአቱ እየደጋገመው ያለው ችግር ለመፍታትና አስቻይ ናቸው ያሏቸውን መፍትሔዎች የሚመራመሩበት ተቋም መኾኑንና ማህበረሰብ ተኮር ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት የሚመራመሩበት ትምህርታዊ ተቋም መኾኑን ከኮሌጁ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ቢድቃ  ሰምተናል።


በዚህ ዘመን የግል የትምህርት ጥራት ጉዳይ አሳሳቢ ከሚባል ደረጃ ላይ የደረሰበት ሁኔታዎች ቢኖሩም ኤግል ኮሌጅ ይህንን ተግዳሮት በጥበብና በእውቀት እያለፈው እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።


ኮሌጁን ያቋቋሙ ሙሁራን  ከዚህ በቀደመ ጊዜ  ከኢ.ፊ.ዲ.ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን  መስርያ ቤት የሰሩ እንደመሆናቸው መጠን የትምህርት ጥራት ችግር ያለበትን ደረጃ በቀላሉ የሚረዱና ችግሩን ለመፍታት እንደ ኤግል ኮሌጅ እየሰሩ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።


ኮሌጁ ለደህንነት ተቋማት ሰራተኞችን ለማረሚያ ቤቶች፣ ፖሊስ አባላት፣ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት መማር ለሚሹ አባለት እንዲሁም መማር ፈልገዉ አቅም ለሌላቸዉ የስኮላርሺፕ እድሎችን በማመቻቸት እያሰተማረ መኾኑን መረዳት ችለናል።


ኮሌጁ የፀጥታ ችግር ያለባቸው የክልል ከተሞች ከፍቷቸው የነበሩት ቅርንጫፎ ኮሌጆችን ለመዝጋት መገደዱ ተናግሯል። በፀጥታና ተያያዥ ጉዳዬች ምክንያት የተዘጉ ኮሌጆቹ የትምህርት ክፍያም ሆነ ሌሎች ከፋይናንስ ጋር የተገናኙ ጉዳዬች መዝጋቱን እወቁልኝ ብሏል።


ኤግል ኮሌጅ በቀጣይ ጊዜያቶችንም በማስተርስ መርኃ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ውጥን ይዞ እየተንቀሰቀሰ እንዳለ የኮሌጁ አመራሮችን ጠይቀን መረዳት ችለናል።