ኤርትራ በባሕር በር ጥያቄ ለድርድር አልቀመጥም አለች

 



የኤርትራ መረጃ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገፅ



ኤርትራ የባህር በር ጉዳይ በተመለከተ ለድርድር እንደማትቀመጥ አስታወቀች።


 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተነሳዉ የባህር በር ጉዳይ ላይ ኤርትራ ለድርድር እንደማትቀመጥ የኤርትራ መንግሥት የመረጃ ሚኒስትር በማህበራዊ ትስስር  ገፁ ፅፏል፡፡


የኤርትራ መንግሥት የመረጃ ሚኒስትር ዛሬ በማህበራዊትስስር ገፁ ባሰራጨው ፅሁፍ በቅርብ ጊዜ ስለ ውሃ እና ስለ ባህር በሮች እንዲሁም ተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳዮች የተነገረው እና የተባለው ቁጥር የለውም ያለ ሲሆን፤ በዚም ያልተገረመ ታዛቢ የለም” ብሏል፡፡


የኤርትራ መንግሥትም እንደኹልጊዜው በእንደዚህ ዓይነቱ ጉዳዮች ላይ ለውይይት እንደማይታደም አስታውቋል።


 ሚኒስቴሩ ይህ ነገር ይመለከተናል የሚሉ ኹሉም አካላት ጉዳዩን እንዳይነኩት በመግለጫው ማሳሰቡን በመረጃ ተጠቅሷል። 


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አርብ ጥቅምት ሀለት በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በተላለፈውና ‹‹ከጠብታ ውኃ እስከ ባሕር ውኃ›› የሚል ርዕስ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ባደረጉት ገለጻ፤ ቀይ ባህርን አስመልክተው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡


በመግለጫቸውም በታሪክ፣ በጂኦግራፊ፣ በዘር (በብሄር) እና በኦኮኖሚ ምክንያቶች የቀይ ባህር ጉዳይ ይመለከተናል። ያሉ ሲሆን ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ እንጂ ቅብጠት አይደለም። አባይና ቀይ ባህር የኢትዮጵያን ልማትና ጥፋት የሚወስኑ የኢትዮጵያ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ናቸው ብለዋል ነበረ ፡፡


(ንጋት ፕሬስ)