በአማኑኤል ክንደያ
የመገጣጠሚያ ቁርጥማ፣ የጡንቻና የኢሚዩኒቲ (መገጣጠምያ) ችግሮችን የሚያክም ተቋም በሐገር ቤት ተከፍተ።
ሩሁም የሩማቶሎጅ እና የዉስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ በመገጣጠሚያ እብጠት (አርተራይተስ) በጡንቻ ህመም እና ከኢሚዩኒቲ ጋር የተገናኙ ችግሮችን ትኩረት አድርጎ የሚሰራ የህክምና ተቋም ነው።
በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው ፤ ሩሁም የሩማቶሎጂ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ የተሰኘ ክሊኒክ ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ሪሂ (Gouty Arthritis) ሩማቶይድ አርተራይተስ (Rheumatoid arthritis) ሉፐስ (SLE/Lupus) የወገብ የትክሻ እና የጉልበት ህመም፤ የመላ ሰዉነት ህመም (Fibromyalgia) እና ባጠቃላይ የዉስጥ ደዌ ህክምና በስፔሻሊስት እና ንኡስ ስፔሻሊስት ሃኪሞች ይሰጣል።
ሩሁም የሩማቶሎጂ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ በአገራችን ያለውን የመገጣጠሚያ፣አያያዥ የጡንቻ ችግሮች ህክምና (Rheumatic and musculoskeletal Disorders ) ያለው የሕክምና ክፍተት ለመሙላት አላማውን ስራ መጀመሩን ሰምተናል።
ፎቶ : ዶ/ር ብርሐኑ ደመላሽ መስራችና ባለቤት
የሩሁም መገጣጠምያ ክሊኒክ ባለቤት ዶክተር ብርሀኑ ደመላሽ የህክምና ማእከሉ ለመክፈት ያነሳሳቸው ሀሳብ በመክፈቻው ንግግር በስፋት ገልፀዋል።
ዶክተር ብርሐኑ ደመላሽ በተለይም በጥቁር አንበሳን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት የህክምና ማእከላት ባገለገሉበት ጊዜ የመገጣጠሚያ ህክምና ለማስፋፋት ያለው ተግዳሮት መመልከት መቻላቸውን አንስተዋል።
ለዚህም የራሳቸውን የህክምና ተቋም በማቋቋም ስራ መጀመራቸውን ገልፀዋል።
በአገር ውስጥ ያሉ የመገጣጠሚያ ህክምና ባለሞያዎች ከሶስት መቶ ቁጥር በላይ የማይበልጡ ናቸው።
በአገራቀፍ ደረ ጃ የተቋቋመው 1999 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ጠቃላይ ሆስፒታል መሆኑን መኾኑን ሰምተናል ።
በአገር ቤት ያለው የመገጣጠሚያ ህክምና ችግር ለመፍታትና የችግሩን ስፋት ለመቀነስ በግለሰብ ደረጃ የሚቋቋሙ የህክምና ማእከላት አስፈላጊነት ዶክተር ብርሐኑ ደመላሽ ሲናገሩ ተደምጠዋል ።
በአገር ቤት በመገጣጠምያ ህክምና ዘርፍ የመጀመሪያ ምሁራን ረድፍ መካከል ከሚሰለፉት በዶ/ር ብርሀኑ ደመላሽ የተቋቋመ ሀገር በቀል የህክምና ተቋም ነው።
ሩሁም የሩማቶሎጂ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ " ጥራት እና ክብካቤ የተሞላበት ህክምና (Royalty Care) በሚል መርህ ሳይንሳዊ መሰረት ያለው ህክምናን ስነ-ምግባር በተሞላበት ሁኔታ ለእያንዳንዱ ታካሚ እንደ ችግሩ መጠን የተገባ አገልግሎት ለመስጠት ወጥኖ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
በመክፈቻ ሰነ-ስርአቱ ላይ ዶክተር አስቻለው ፣ የኮተቤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሀነመስቀል ቀና ፣ ዘነበ መላኩ ፣ዶክተር አብዱረዛቅ አህመድ ፣ ዶክተር ሲሳይ ሲርጉ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች የመክፈቻ ሰነ ስርአቱ ተገኝተዋል ።
ክሊኒኩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ የህክምና ባለሙያዎች ማህበራት ፣ ባለድርሻ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
(ንጋት ፕሬስ)
ህክምናውን ማግኘት ለምትሹ ሁሉ በተጠቀሰው አድራሻ መሰረት ማግኘት ትችላላችሁ ።
አድራሻ:- ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ አካባቢ ፤ ከቂርቆስ ኮንዶሚኒየም ወርድ ብሎ ፤ ቂርቆስ ቴሌ ጎን።
ስልክ:- 0973125594/ 0973125609
- ጎግል ማፕ: https://maps.app.goo.gl/uKd5gPvx9pqD9jnK8
- ቴሌግራም: https://t.me/RheumIMSC
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/profile.php?id=100086453364046
:https://www.tiktok.com/@rheumrheumatology?_t=8dBFT5fLYYw&_r=1
-ኢንስታግራም:https://instagram.com/rheum_medical_services?igshid=NTc4MTIwNjQ2YQ==



