ኮስሞፖሊተን ሪልስቴት የገነባውን አፓርታማ ለደንበኞቹ ማስረከቡ ተናገረ።

 ቢዝነስ





በቤት ልማት ስራ ላይ የተሰማራው ኮስሞፖሊተን ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ ማህበር አዲስ አበባ  ያስገነባው አፖርታማ አስመረቀ።


በመዲናይቱ ቦሌ ሩዋንዳ አከባቢ በ700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ  አፖርታማ ገንብቶ ለደንበኞቹ ያስረከበ ሲኾን የተገነባው አፓርታማ ባለ አስራ አንድ ደብር (G+11) ነው ። በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ለደንበኞቹ የቁልፍ ርክክብ አድርጎ በውሉ መሠረት ቤቶቹን ማስረከቡን ተመልክተናል ።


ተገንብቶ ለገዢዎች የቀረበው ይኸው አፓርታማ ዘመን አፈራሽ የኾኑ የስራ ማቀለጣጠፍያ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት ሲኾን የሀያ አራት ሰአት የመብራት አገልገሎት መስጠት የሚችል የኤሌክትሪክ አቅርቦት የተገጠመለት ነው ተብሏል ። 

በተጨማሪም ህንፃው የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም፣ ሳውናና ስቲም አገልግሎቶችን የሚሰጥ መኾኑን ከኩባንያው አመራሮች ተረድተናል ።




ኮስሞፖሊተን ሪልስቴት ከዚህም በቅርቡ ኦሎምፕያ አከባቢ ባለ አሰራ ሰባት(G+17) ህንጻና  በፒያሳ ካቴድራል አካባቢ ደግሞ ለሱቅና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የገበያ ማዕከል ግንባታ እንደሚጀምር ሰምተናል። 


ለሽያጭ እየቀረቡ የሚገኙት አፓርታማዎች በዋጋቸውን በተመለከተ  ደረጃ ተመጣጣኝና ምክንታዊ በኾነ መንገድ የቀረቡ ናቸው ተብሏል ።


ኮስሞፖሊተን ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ ማህበር ተመስርቶ አገልገሎት መስጠት ከጀመረ አምስት አመታት ያስቆጠረው ሲኾን፣ በመዲናችን አዲስአበባ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግርን ለማቃለል የራሱን አሻራ እያሳረፈ ያለ የቤት ልማት ስራ ላይ የተሰማራ አገር በቀል ኩባንያ ነው።




ድርጅቱ ከቤት ልማት ኢንቨስትመንት በተጨማሪም በአስመጪና ላኪነት፣ በቤት እና በቢሮ እቃዎች፣ በወረቀት ማምረት ጨምሮ በትራንስፖርት የስራ ዘርፍ ላይ ሰማርቶ  ለደንበኞቹ  አገልግሎት መስጠት ላይ ይገኛል። 


በሜትሮፓሊተን ሪል ስቴት ከዚህ በኃላ በሚኖሩት የኢንቨስትመንትና የቤት ልማት ዘርፍ የራሱን አሻራ ለማስቀመጥ ውጥን ይዞ እየተንቀሳቀሰ  እንዳለ የድርጅቱ ኃላፊዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል ።


የመርሀ-ግብሩ  አዘጋጅ እና የሚድያ ፣የህዝብ  ግንኙነት  ሥራውን ያከናወነው  ተወዳጅ  ሚድያ  እና ኮሚኒኬሽን  ሲሆን በዕለቱም በተወዳጅ ሚድያ  ስራ አስኪያጅ እዝራ እጅጉ አማካኝነት  ጋዜጣዊ  መግለጫ ተሠጥቷል ።

(ንጋት ፕሬስ)