ቢዝነስ/ ዜና
ሮያል ፎም የኢ ቢ ኤስ ቲቪ ሾው አቅራቢዋና የማስታወቂያ ባለሞያ የሆነቺውን ሉላ ገዙን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መምረጡ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን እወቁት ብሏል።
ሉላ ገዙ ከድርጅቱ ጋር ለሚቀጥሉት አራት አመታት የተስማማች ሲኾን የማህበራዊ ሚድያ፣ በቢልቦርድና እንዲኹም በተለያዩ መገናኛ አውታሮች ኩባንያው የሉላ ገዙን ምስል የሚጠቀም መኾኑን በስምምነቱ መርኃ ግብሩ ላይ ሲነገር ሰምተናል ።
ሉላ ከዚህ በቀደመ ጊዜ በተለያዩ የማስታወቅያ ሰራዎች በመስራት የምትታወቅ ባለሞያ ሰትኾን፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲኽ ደግሞ በኢ ቢ ኤስ ቴሌቭዥን በመዝናኛ ክፍል የተለያዩ ዝግጅቶች ታቀርባለች።
አሁን ላይ የሮያል ፎም የብራንድ አምባሳደር ሆና መሾሟን በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተን ማረጋገጥ ችለናል።
ሮያል ፎም እና ፈርኒቸር የተሰኘውን ንግድ ድርጅት ከተመሠረተ ከ 15 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲኾን የፎም እና የፈርኒቸር ምርትን ጨምሮ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ውስጥ ተሰማርቶ የሚገኝ አገር በቀል ኩባንያ ነው።
ኩባንያውከተሰማራባቸው የምጣኔ ሀብት ክንዋኔዎች መካከል የቡና ኤክስፖርት ሪልእስቴት፣ ኮንስትራክሽን፣ በሆቴል (ኢዮሜር ሆቴል)፣ ጨርቃ ጨርቅና በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ የተሰማራ ንግድ አቀላጣፊ ድርጅት ነው።
ኩባንያው ሉላ ገዙን ሮያል ፎም አምባሳደር አድርጎ ሲሾማት ሉላ በአገራቀፉ ደረጃ ካላት መልካም ስምና ተቀባይነት አንፃር መኾኑን ድርጅቱ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ከሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተረድተናል ።
ኩባንያው በጥቅምት 30/ 2016 ዓ/ም በኢዮሜር ሆቴል ባከናወነው የፊርማ ሰነሥርአት ላይ የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ሾው አቅራቢዋ ሉላ ገዙን ለአራት አመታት የሮያል ፎምና ፈርኒቸር ብራንድ አምባሳደር ለመሆን የሚያስችላትን ስምምነት አስፈርሟታል ።
ሮያል ቢዝነስ ግሩፕ በውስጡ ከያዛቸውና ከሚያቀለጣጥፋቸው የቢዝነስ አይነቶች አጠቃላይ ስድስት ናቸው ተብሏል።
(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)


