ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፀጋውን ሸክ አሊ ሁሴን አላሙዲንን ጎብኝቻለሁ ማለታቸውን ፅህፈት ቤታቸው ካሰራጨው ዘገባ ተረድተናል
ባለ ሀብቱ ሸህ አላሙዲንን ለማስፈታት ከሳኡዲ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ለመደራደር ውጥን እንደነበራቸው ከዚህ ቀደም ዐብይ አህመድ ሲናገሩ ነበር።
ሆኖም አብይ የድርድራቸው መጨረሻና መጀመርያ ምን ላይ እንደደረሰ ሳይታወቅ አመታት አልፈዋል።
አብይ ከሳዑዲ መንግስት ባለስልጣናት ጋር መልካም ግንኝኑነት እንዳላቸው ቢናገሩም፣ እስካሁን ድረስ ባለሀብቱ አላሙንን ከእስር በሚፈቱበት ዙርያ ጠብ ያለ ነገር አላመጡም፤ ቢን ሳልማንም በበኩላቸው በባለሀብቱ እንዲፈቱ የቀረበላቸው ጥያቄ በጄ አላሉም ።
ከአመታት በኃላ ግን አብይ ሼህ አላሙዲንን ሳኡዲ ሪያድ ከተማ ተገኝተው በግንባር አግኝተዋቸዋ። ባለሀብቱ ከእስር ይፈቱ አይፈቱ በሚለው ዙርያ ግን አብይም ሆኑ ፅፈት ቤታቸው እስካሁን ድረስ ያለው ነገር የለም።
አላሙዲንን በተመለከተ ከሳኡዲ ያሉ ምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ የምናደርስ መኾኑን እንገልፃለን።
-Advertisment -
(ንጋት ፕሬስ)

