የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ በሴትኛ አዳሪነት ንግድ ስራ ህይወታቸውን የሚገፉ የመዲናዋ ሴቶች የሚቀይር ፕሮጀክት ስራ ላይ አውላለሁ አለ

ማህበራዊ /ዜና 


  ፎቶ; ወይንሸት ዘሪሁን የመዲናዋ የሴቶች ፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች  ቢሮ ሓላፊ


የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ በአንድም በሌላ ምክንያት በወሲባዊ ንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው ለሚገኙ ሴቶች መደበኛ ህይወት የሚጀምሩበት ፕሮጀክት በተያዘው በጀት አመት ሊጀምር መኾኑን እወቁልኝ ማለቱን ከቢሮው ሓላፊ ወይንሸት ዘሪሁን ሰምተናል።


ሓላፊዋ ወይንሸት ዘሪሁን ፕሮጀክቱ አላማ ሲያስረዱ በየአመት አሰር ሺ ለሚደርሱ በመዲናዋ ለሚገኙ በወሲብ ንግድ ላይ ኑሯቸውን የሚያሻሽሉበት መኾኑን ጠቅሰው የተለያዩ ሰነልቦናዊና ማህበራዊ ተሀድሶ የሚያደርጉበት መኾኑን ነግረውናል።


ፕሮጀክቱ ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ የሚጠይቅ በመኾኑ በመዲናይቱ የሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረገው ትብብር ህይወታቸውን የሚያሻሽሉበት መርሐግብር  ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች መጀመሩን ከቢሮ ሓላፊዋ ወይንሸት ዘሪሁን ተረድተናል ።


በከተማዋ የተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ በወሲባዊ ንግድ ላይ ህይወታቸውን የሚገፉ ሴቶች እንዲሻሻል  በብርቱ እየሰራ መኾኑን ከአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር የሴቶች  ፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ለማወቅ ችለናል ።



     ፎቶ; ሁርያ አሊ የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዬች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ


ቢሮው ከዚህ ተጨማሪም ሴቶች ለሚደርስባቸው አካላዊ ፣ ስነልቦናዊ ጥቃቶች ራሳቸውን የሚከላከሉበትና መብትና ደህንነታቸውን በማስጠበቅ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ መብቶቻቸውን የሚያስጠብቁት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰራዎችን ሲሰራ መቆየቱንም ገልጿል ።


የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰማሚ ቴክኖሎጂ ተግባራትን እያከናወነ መቆየቱንም የቢሮ ሓላፊዋ  የነገሩን ሲኾን፣ ይህንኑ ውጥን እንዲሳካም የሴት አደረጃጀቶችን በማቀናጀት በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ እያደረገ መቆየቱንም ተናግረዋል።


ከዚሁ በተጨማሪም አረጋውያን ና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ በከተማዋ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ ላይ መኾኑንና ተደራራቢ ህመም ላለባቸው ከ64 ሺ በላይ ዜጎችን ቀጥታ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ተግባራት እያከናወንኩ እገኛለሁ ማለቱን ከቢሮው ባገኘነው መረጃ ማረጋገጥ ችለናል።


ከቢሮ ሓላፊዋ ወይንሸት ዘሪሁን ለመረዳት እንቻልነው ከኾነም በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ሴቶችን ማህበራዊ ፣ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንቅስቃሴዎች በብርቱ እየሰራ መኾኑን ነው።



የአዲስአበባ ከተማ ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የመዲናዋ ነዋሪዎች ምቹና ተስማሚ ከተማ እንድትኾን የተለያዩ ሐላፊነቶችና ተልእኮዎችን ተሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ መንግሥታዊ ተቋም መኾኑን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን በተደጋጋሚ በሚሰጣቸው ማብራርያዎችና መግለጫዎችን መረዳት ተችሏል።


                   የፓናል  ውይይቱ ተሳታፊዎች 

 

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ቦሌ ዓለም ሲኒማ ጎን በሚገኘው ፍሬንድሺፕ ዓለም አቀፍ ሆቴል    የኢፌደሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የከተማው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በየዘርፉ የላቀ ወጤት ካስመዘገቡ ስኬታማ ሴቶች ጋር የልምድ ልውውጥና የፓናል ውይይት በቢሮው አዘጋጅነት መደረጉን ተመልክተናል ።


በመርሃ -ግብሩ ላይ በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ሴቶች፣ በዩኒቨርስቲ ትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ሴቶችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ በጎ ልምድ ያላቸው ሴቶች የሕይወት ተሞክሮና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት መረሀ ግብር ተደርጓል።


ቢሮው በ2015 ዓ/ም  በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሴት ተመራቂዎችና የ12ኛ ክፍል  ሀገር ዓቀፍ ፈተናን ተፈትነው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች  የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አከናውኗል። 


 

በመርሃ ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሁሪያ አሊ ሴቶች በዕውቀትና ክህሎት  የዳበሩ እንዲሆኑ ዓለም በደረሰበት መንገድ  መሄድ እንዲችሉ  በትጋት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀው ውጤቱም በተማሪዎች ህይወት ሁሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት  ለተማሪዎቹ  መልዕክት ማስተላለፋቸውን  ሰምተናል።


                         -Advertisment-



(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)