መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ አልቀበለውም አለ

ፎቶ :- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ 

በአማራ ክልል የህዝቡን ጥያቄ መፍታት የሚችል አዲስ አመራር መደራጀቱን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ገለጹ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር  ለገሰ ቱሉ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በተለይም በአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ፣ የግብርና ስራ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአማራን ህዝብ ጥያቄ ሽፋን በማድረግ ጽንፈኛ ቡድኑ የራሱን እኩይ አላማ ለማሳካት ጥረት ማድረጉን ጠቅሰው መንግስት የተጠናከረ ህግ የማስከበር ስራ በማከናወን በክልሉ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። 

በክልሉ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ በወቅቱ መደበኛ ህግ ማስከበር እንደማይቻል በመረጋገጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት እና የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ጠቅላይ መምሪያ እዝ በማደራጀት የህግ ማስከበር ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ እዙም በልዩ ልዩ አደረጃጀቶች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ተግባር ተገብቷል ነው ያሉት።

በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ማፍረስ ዓላማ በማድረግ መንቀሳቀሱን ጠቅሰው መንግስት ወደ ህግ ማስከበር በመግባቱ አደጋውን መቀልበስ መቻሉን ገልጸዋል።

የክልሉም አመራር በአዲስ መልክ ተደራጅቶ የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ቡድኑ በመበታተኑ ወደ ተራ ሽፍተኝነት ተግባር መውረዱን ጠቅሰው በመንግስት የሚወሰደው የማጽዳት እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 3 ሺህ 200 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በመጀመሪያው ዙር 1 ሺህ 51 ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን ገልጸዋል።

በሁለተኛው ዙር ደግሞ 931 ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት አያያዝ መልካም መሆኑን ማረጋገጡንም ተናግረዋል። 

በመጪዎቹ ጊዜያትም ተበታትኖ የዝርፊያ ስራ ላይ የተሰማራውን ጽንፈኛ ቡድን የማጽዳት ስራ በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን ያወጣው መግለጫ በተጨባጭ መረጃ ያልተደራጀ፣ ሚዛናዊነት የጎደለው በመሆኑ ኮሚሽኑ ተገቢውን እርምት ያደርጋል ተብሎ ተስፋ ይደረጋልም ብለዋል።

በአማራ ክልል የህዝቡን ጥያቄ መፍታት የሚችል አዲስ አመራር መደራጀቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

(ንጋት ፕሬስ )