ምርት የሚደብቁና የዋጋ ንረት እንዲባባስ እያደረጉ ያሉ አካላት ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ነው

ዜና




 የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የገበያ ትስስር በመፍጠር የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በቀጥታ ለሸማቾች እንዲደርስ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ መኾኑን ተናገረ  


በአዲስአበባ ከተማ ውስጥ ከ150 በላይ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና 11 የሸማች ዩኒየኖች የተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎችን እያከናወኑ የሚገኙ መኾናቸውን በዋሽንግተን ሆቴል ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው የምክክር መድረክ ሠምተናል።


በዚሁ መድረክ ተሳታፊዎች መካከል ከኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ ከአስመጪዎችና ከኅብረት ሥራ ዩኒየኖች መኾናቸውንና ኮሚሽኑ በገበያ ትስስርና ምርት አቅርቦትና ተያያዥ ጉዳዬች ዙርያ  ውይይት አካሂዷል። 

 


               የውይይቱ ተሳታፊዎች 



የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የኾኑት ሀብተየስ ዲሮ ለአገርዐውስጥ መገናኛ ብዙሐን እንደገለጹት ከኾነም  የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች በቀጥታ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው መኾኑን ሲናገሩ ሰምተናል ። 

 

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንደሚሉት የአገር ውስጥ አምራቾችና አስመጪዎች በቀጥታ ከሸማቹ ጋር በመገናኘት ግብይት እንዲያካሂዱ የሚያስችል የገበያ ትስስር ለማጠናከር በብርቱ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል ። 

 

ኮሚሽኑ ከያዛቸው ውጥኖች መካከልም ነጋዴዎች በግብርና ምርቶች ምንም ዓይነት እሴት ሳይጨምሩ ዋጋ ብቻ በመጨመር የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እያደረጉ ያሉትን ህገ-ወጥ የደላሎች እንቅስቃሴ ይቀንሳል የሚል እምነት እንዳላቸው ሀብተየስ ዲኖ አስረድተዋል ።

 

የገበያ ትስስሩ  ሕገ-ወጦች ትርፍ ለማጋበስ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን የሚደብቁ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረበት መኾኑን ከምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለመረዳት ችለናል። 

 

በመዲናዋ ከ150 በላይ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና 11 የሸማች ዩኒየኖች እንደሚገኙም የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)