የግምጃ ቤት ሰነድ በባህሪው ዝቅተኛ እና ቋሚ ወለድ የሚታሰብበት አንዴ ለሽያጭ ከቀረበ በኋላ ዋጋ ንረትን ከግምት በመክተት የማይለዋወጥ በመሆኑ ስጋት የሚፈጥር ሲሆን የመንግስት መተማመኛ ያለው እና በካፒታል ገበያ በኩል በቀላሉ ለሌላ ሰው መሸጥ የሚችል መሆኑ እንደ እድል ያስቆጥረዋል፡፡እነኚህና ተያያዥ ጉዳዬች ዙርያ የንጋት ፕሬስ ዋና አዘጋጅ አማኑኤል ክንደያ ሰብሰብ አድርጎ ያቀርብላቹሀል። ዝርዝሩን አንብቡት...
መንግሥታት በኹለት ምክንያት የግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ ያቀርባሉ።
የመጀመሪያዊ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመስራት የካፒታል ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት መንግስት ገቢ ከመሰብሰቡ በፊት ፕሮጀክቶቹ በፋይናንስ እጥረት እንዳይቆሙ ከገበያው በወለድ በመበደር ለማከናወን በማሰብ ነው።
በኹለተኝነት በገበያው ያለውን የገንዘብ አቅርቦት እና ፍላጎት ለማመጣጠን ሲል የገንዘብ አቅርቦትን ለመጨመር ባሰብ ጊዜ ከገበያው ሰነድ በመሸጥ መበደሩን ሲያቆም የገንዘብ አቅርቦት እንዲቀንስ ከገበያው በሰነድ በመበደር ገንዘቡን በዘዴ ይሰበስባል "ሰነድ በሰዎች እጅ ገንዘብ በማዕከላዊ ባንክ እጅ ይገባል ማለት ነው" ነው፡፡
መንግሥታት የግምጃ ቤት ሰነድ በቀጥታ በራሳቸው ቻናል ለሽያጭ በጨረታም ሆነ ያለጨረታ ሊያቀርቡም ሆኑ በሁለተኛ ገበያ(በካፒታል ገበያ) በኩል ለሽያጭ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ መንግስት ለሸጠው ሰነድ መተማመኛ የሚሆን ሰርተፍኬት ለሰነድ ገዢ ግለሰብ ወይም ድርጅት ይሰጣል፡፡
የግምጃ ቤት ሰነድ ለአጭር ጊዚያት ማለትም ከ28 ቀን እስከ 365 ቀናት የቆይታ ጊዜ ሊኖራቸው ሲችል እንደቆይታ ጊዚያቸው የወለድ መጠናቸው ሊለያይ ይችላል፣ የሰነዱ የክፍያ ወቅት (Maturity) ሲደርስ መንግስት ወለዱን በማሰብ ክፍያ የሚፈጽም ይሆናል፡፡
የግምጃ ቤት ሰነድ ወለድ አስተሳሰቡ ኹለት አይነት ዘዴ ሊኖረው ይችላል (ወለድ ማስቀመጥ (ለምሳሌ ለተገዛው ሰነድ መጠን 3 ከመቶ ወለድ ማሰብ እንደማለት) አልያም የመሸጫ እና የመክፈያ መጠን ማስቀመጥ (ለምሳሌ የ100 ብር ሰነድን በ95 ብር እንደመሸጥ አይነት (በ95 የገዛ ሰው 100 ብር ተደርጎ ይከፈለዋል እንደማለት ነው)፡፡
ሃሳቡን በቀላሉ እድትረዱት የኢትዮጲያ ልማት ባንክ የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ቦንድ ለህዝብ አቅርቦ ሰዎች በቻሉት መጠን በሙሉ ገዝተዋል ከአምስት ዓመታት (Maturity) በኋላ ወለድ በማሰብ ክፍያ ሲፈጽም የምትመለከቱት የእዳ ሰነድን ይወክላል (የህዳሴው ግድብ የግምጃ ቤት ሰነድ ሳይሆን እንደቆይታው በኖት እና በቦንድ ውስጥ ሊጠቃለል ይችላል (በኢትዮጲያ ሁኔታ አሁን ላይ የግምጃ ቤት ሰነድ ለልማት ድርጅቶች (የፋይናንስ ተቋማትም ይጋበዛሉ) በሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን ወደፊት የስቶክ ገበያው ሲከፈት ለጠቅላላ ገበያው ሊለቀቀቅ ይችላል፡፡
የግምጃ ቤት ሰነድ ከሌሎች የመንግስት የእዳ ሰነዶች አይነት የአጭር ጊዜ እዳ ነው፡፡ ሌሎቹ Treasury Note ከ1- 10 ዓመት ቆይታ ያለው ብድር ሲሆን Treasury Bond እስከ 30 ዓመት ሊቆይ የሚችል እዳ የሚይዙ ናቸው፡፡
የግምጃ ቤት ሰነድ ሻጩ መንግስት በመሆኑ ላይከፈል ይችላል የሚል ስጋት የሌለበት ነው፡፡ አንድ ሰነድ የገዛ ሰው የመክፈያው ወቅት እስኪደርስ ወለድም ሆነ የከፈለውን ገንዘብ ባያገኝም ለሌላ ሰው በካፒታል ገበያ በኩል የመሸጥ እድል ግን ይኖረዋል፡፡
የግምጃ ቤት ሰነድ በባህሪው ዝቅተኛ እና ቋሚ ወለድ የሚታሰብበት አንዴ ለሽያጭ ከቀረበ በኋላ ዋጋ ንረትን ከግምት በመክተት የማይለዋወጥ በመሆኑ ስጋት የሚፈጥር ሲሆን የመንግስት መተማመኛ ያለው እና በካፒታል ገበያ በኩል በቀላሉ ለሌላ ሰው መሸጥ የሚችል መሆኑ እንደ እድል ያስቆጥረዋል፡፡
(ንጋት ፕሬስ )
