ኢትዮጵያ ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት ላበረከተችው አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ ማዕከል በአዲስአበባ ሊገነባ ነው

ዲፕሎማሲ /ዜና


Ambassador melese alem, mouth peace of minster of forigne affairs 


በአዲስ አበባ የሚከፈተው የዓለም የጥቁር ህዝቦች የታሪክ የቅርስና የትምህርት ማዕከል ኢትዮጵያ ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት ላበረከተችው አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ መግለጫው ለጋዜጠኞች ተናግሯል ፡፡


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።


አምባሳደር መለስ በመግለጫቸው የዓለም የጥቁር ህዝቦች የታሪክ የቅርስና የትምህርት ማዕከል በኢትዮጵያ ሊከፈት መሆኑን እወቁት ብለዋል።


መለስ አለም ማዕከሉ በአሜሪካ ካሪቢያንና በሌሎች ዓለም ላይ ያሉ ጥቁር ህዝቦች የጥናትና ምርምር ተቋማትን ያቀፈ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡


በመጪው ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ዋና መቀመጫውን ኢትዮጵያ ማድረጉን በይፋ ያሳውቃል ያሉት ቃል አቀባዩ ይህም ኢትዮጵያ ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት ላበረከተችው የላቀ አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ ነው ብለዋል።


የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት፣ የራሷ ፊደል ባለቤት፣ የስልጣኔ ማዕከል፣ የአፍሪካ ህብረት መስራችነትና ሌሎችንም ልዩ መገለጫዎች ታሳቢ በማድረግ ኢትዮጵያ ለማእከሉ መቀመጫነት የተመረጠች መሆኑንም ጠቅሰዋል።


እነዚህንና ሌሎችንም እሴቶች ታሳቢ በማድረግ የሚቋቋመው የዓለም የጥቁር ህዝቦች የታሪክ የቅርስና የትምህርት ማዕከል ለአዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ተጨማሪ ነገር ይዞ የሚመጣ መሆኑንም አምባሳደር መለስ ገልጸዋል።


የኮንፍረንስ ቱሪዝምን በማስፋት እና የጎብኝዎችን ቁጥር በመጨመር ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም አስረድተዋል ።


ከ20 በላይ የፈረንሳይ ታላላቅ የግል ኩባንያዎች ከህዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት በኢትዮጵያ የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ብለዋል።


ቃለ አቀባዩ በሳምንታዊ መግለጫቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተሳተፉበት የሳውዲ አፍሪካ ጉባኤ ኢትዮጵያ በዓለም መድረኮች ላይ ያላትን ተደማጭነት ያሳየችበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡


(ንጋት ፕሬስ )