በቻይና አገር ታዋቂ የምግብ አምራች ኩባንያ የሆነው ኤስ (ACE) አርቲስት ሀናን ታሪቅን አምባሳደር አድርጎ መምረጡን ተናገረ


 ሀናን ታሪቅ የኩባንያው የብራንድ አምባሳደር ሆና ስትሰራ ለሁለት አመታት አስር ሚልየን ብር እንደሚከፈላት ከተዋናይቷ አንደበት ሰምተናል።


ድሪመር  ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ኤስ (ACE) የተሰኘው መሰረቱ ቻይና አገር ያደረገው ይኸው ኩባንያ የተመሰረተው እኤአ በ 1979 ገደማ ሲኾን እድሜ ጠገብ ከሚባሉ ድርጅቶች ተርታ ይሰለፋል።


 ድሪመር  ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ኤስ (ACE) አርቲስት ሀናን ታሪቅ ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የኩባንያው የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን በአዲስአበባ በስካይ ላይት ሆቴል በተደረገው የፊርማ ስነስርዓት ተናግሯል ።


ይኸው ቻይና በቀል ምግብ አምራች ኩባንያው  የዳበረ የኢንዱስትሪ ልምድ ያለው ሲኾን የምርቶች ስብጥር በአለም አቀፍ የገበያ ስርአት ውስጥም ቢሆን የታወቀ ኩባንያ መኾኑን ከተቋሙ ድህረ ታሪክ ለመረዳት ችለናል ። 




ይኸው የቻይና አገር ምግብ አምራች ኩባንያ "ኢትዮጵያዊትዋን አርቲስት ሀናን ታሪቅን ምርቶቼን ታስተዋውቅልኝ መገለጫዬም ትሁንልኝ" በማለት ታህሳስ 03 ቀን 2016 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ለሁለት አመታት የሚቆይ ውል አስረዋል።


ኩባንያው እንደ ኩኪስ፣ ካንዲስ እና ቾኮሌት ያሉ ጣፋጩ ምግቦችን የሚያወርት ሲኾን  በተለይም “ካስተርድ ፓይ" የተሰኘውን የምግብ አይነት እውቅና ካተረፈባቸው ምርቶች በግንባር ቀደምነት ይታወቅለታል። ከፍ ያለ የኮኮብ ማእረግ ስም ካላቸው ምርቶች  መካከል ተጠቃሽ ነው ይባላል።


ድሪመር  ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ባቋቋመው ዘመናዊ የምግብ ማቀነባበሪያ ኮምፕሌክስ እማካይነት "ኤስ” (ACE) በሚል ብራንድ  የታሽጉ  ጣፋጭ  ኬክ ምግቦችን እያመረተ በመላው ኢትዮጵያ ባሉት ወኪሎች አማካኝነት እያከፋፈለ ሲገኝ ድርጅቱ  ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ፣ በምርት አቅርቦትና በገቢ ግብር በኢኮኖሚው ውስጥ የድርሻውን አስተዋፅአ እያበረከተ ነው ተብሏል ።




ካለፈው በጀት አመት አንስቶም ኩባንያው (ኤስ(ACE) በአፍሪካ ገበያ በንቃት ንግዱን እያቀለጣጠፈ መኾኑን ሰምተናል። ይኸው ቻይና በቀል ምግብ አምራች ኩባንያ በአፍሪካ አንዳንድ አገራትም የማምረቻ ማእከሎች አሉት ተብሏል። በኢትዮጵያ፤ ናይጄሪያ፣ ኮትዲቮር፣ ስኔጋል፣ ታንዛኒያ ባሉ አገራትንም ፋብሪካ ተክሎ በስፋት ቢዝነስ እያቀለጣጠፈ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያዊትዋ አርቲስት ሀናን ታሪቅ ጋር በነበራቸው የፊርማ ስነስርዓት ላይ ኩባንያውን የሚገልፁ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ከተሰራጩ ፅሁፎች አንብበናል ።


ድሪመር  ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ኤስ (ACE) ብራንድ ምርቶቹን በስፋት ለማስተዋወቅና ስርጭቱን ለማስፋት የሚያስችልና ከስድስት ወር እስከ አንድ-አመት የሚዘልቅ የ'ኮርፖሬት ብራንድ ፕሮሞሽን" እቅድ አውጥቶ ለመተግበር ዝግጅት ያጠናቀቀ ሲሆን ለዚህም 50 ሚሊዮን ብር መመደቡንም በበርካታ ፊልሞች ብቃትዋን ያስመሰከረቸው ኢትዮጵያዊት አርቲስት ሀናን ታሪቅ ጋር በጋራ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል ።


የፊርማ ስነስርዓቱንም በአገር ውስጥ ከፍተኛ እቅና ካላቸው የመዝናኛ ዘርፍ ጋዜጠኞች የአዋሽ Fm ዳይናሚክ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ በኾነቺው ጋዜጠኛ አለምነሽ ኩምሳ መመራቱንም ከቦታው ተገኝተን ታዝበናል።


(ለንጋት ፕሬስ  አማኑኤል ክንደያ)