የትምህርት ስርአቱ ለማገዝ የተዘጋጀ መተግበርያ ይፏ መሆኑ ተሰማ

 ዜና


     photo : በአለም ሲኒማ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ



"ዮቶፒያስ ስቱደንትስ" የተሰኘ የትምህርት አጋዥ መተግበርያ ይፏ መኾኑ ተነገረ


መተግበርያው ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንዲኾን ተደርጎ የተሰራ መኾኑን ሠምተናል።


 ይኽን የሰማነው አዘጋጆቹ በአለም ሲኒማ በሰጡት መግለጫ ነው።


ዩቶፒያስ ስቱደንትስ የተሰኘው መተግበሪያ      በትምህርት ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በኩል አገልግሎት እንዲሰጥ ፍቃድ አግኝቷል ተብሏል።


ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አርቲስት ሙሉአለም ጌታቸዉ እንዲሁም የተለያዩ የሚዲያ አካላት  በተገኙበት  አለም ሲኒማ በሚገኘው አዳራሽ  ይፋ ተደርጓል።




መተግበርያው በአማርኛ፣ኦሮምኛ፣ሶማልኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ነው።


ትኩረቱን በትምህርት ዘርፍ በተማሪዎች ዘንድ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲያመጣ የተዘጋጀ መኾኑን ከአዘጋጆቹ ተረድተናል።


ዮቶፒያስ የተሰኘው መተግበርያ  ከ2017 እስከ 2022 ለሚማሩ ሁሉ የ12ኛ ክፍል የመግቢያ ፈተናዎችን እስከ መልሶቻቸው ልምምድ እንዲያደርጉበት ያስችላል ተብሏል።


 ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ አጋዥ መፅሀፍቶችን ጨምሮ በ24 ስዓት ጥያቄዎችን የሚመልስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Al) መምህር  አለው።


በዚህም መሰረት ተማሪዎች ስለዚህ መተግበሪያ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ጠቀሜታውን ተረድተው ራሳቸውን ለፈተና ብቁ እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል።


 መተግበሪያው ለአጠቃቀም ምቹ በመሆኑ ተነግሯል።


የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አርቲስት ሙሉአለም ጌታቸው ነው።


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)