ደመቀ መኮንን በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ላጎደልኩት ነገር ሁሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ አሉ

ዜና/ፓለቲካ 


         ደመቀ መኮንን የቀድሞ የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት 



 ደመቀ መኮንን ትናንት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ላጎደልኩት ነገር ሁሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል።


ትናንት 'ለት ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ የምክትል  ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአመራር ዘመናቸው -አጉድየዋለሁ- ላሉት ነገር በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።


በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን የሀገረ መንግስት ግንባታ ፈተና ለመሻገር ሕገ መንግስትን ከማሻሻል ጀምሮ ሌሎች ስብራቶችን ማረም እንደሚያስፈልግም ደመቀ ሲናገሩ ተደምጠዋል ።


ደመቀ፣ እርሳቸው በነበሩበት የአመራር ዘመን ከሁሉም በላይ ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ይህ አይነቱ አካሄድ በትውልድ ቅብብሎሽ እና ስልጡን አግባብ መቀጠል ሲችል እንደሆነ ምኞታቸውን ገልጸዋል።


ደመቀ ፣ ለብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባደረጉት ንግግር ለ31 ዓመት ተኩል በአመራርነት ተከትሎ ከኃላፊነት ለመሰናበት ያቀረቡት ጥያቄ  በፓርቲው ተቀባይነት በማግኘቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።


ደመቀ፣ ጥያቄያቸው ምላሽ በማግኘቱም በጣም ዕድለኛ ነኝ ሲሉም ተደምጠዋል።


(ንጋት ፕሬስ )



                       -Advertisement-