አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በአገር ውስጥ ያሉ የጃዝ ሙዚቃ ወዳጆች ጋር በግንባር የሚገናኝበት ዝግጅት ሊደረግ ነው

 ዜና/ ኪን


          ፎቶ; [መጎስ መኮንን]   አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ ግዮን ሆቴል 



አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በአገር ውስጥ ያሉ የጃዝ ሙዚቃ ወዳጆች ጋር በግንባር የሚገናኝበት ዝግጅት ሊደረግ ነው


 አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በአገር ውስጥና በአለማቀፉ ደረጃ ኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ በመቀመር ፈር ቀዳጅ ነው።


አርቲስቱ በጃዝ ሙዚቃ ዘርፍ ከ50 አመታት በላይ የተለያዩ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቀምሯል።


ዝግጅቱ ታዋቂ ኤቨንትስ ተዘጋጅቶ የቀረበና ታዋቂ ስዎችን ከአድናቂዎቻቸው ጋር በአንድ ላይ ተሰባስበው የሚያመሹበት የሚጨዋወቱበት መርኃ ግብር መኾኑን ሰምተናል።


የታዋቂ ኤቨንትስ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሳሙኤል አበራ ዝግጅቱን በግዮን ሆቴል በአፍሪካ ጃዝ መንደር የካቲት 9/2016 ዓ/ም እንደሚካሄድ በተሰጠው መግለጫ ተናግሯል።


ሳሙኤል አበራ እንደሚለው ዝግጅቱ በደማቁ እንዲከወን አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገናል ብሏል።


አርቲስት ሙላቱ በዚህ ዝግጅት የሚታደመው ጀርመን አገር የሙዚቃ ዝግጅቱ ማግስት መኾኑን የታዋቂ ኤቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ ሳሙኤል አበራ   ለጋዜጠኞች ተናግሯል።


ሙላቱ አስታጥቄ በኢትዮጵያ ውስጥ በቂ አክብሮትና አድናቆት ካላገኙ የኢትዮ ጃዝ አባት ነው።


በአለማቀፍ ደረጃ ጉድ ያሰኙ የሙዚቃ ድግስ በማዘጋጀት ተፅዕኖ ያተረፈ ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ሰው መኾኑ ይታወቃል።



የሰራው የክብር ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ የካቲት 9/2016 ዓ/ም በግዮን ሆቴል በሚገኘው በአፍሪካ ጃዝ መንደር ከአድናቂዎቹ ጋር ተገናኝቶ ራት ይበላል ፊርማውንም ያስቀምጣል።


ታዋቂ ኤቨንት ዝነኞችን ከአድናቂዎቻቸው ጋር የማገናኘቱን ረገድ ሲያከናውን ለሁለተኛ ጊዜ መኾኑን መረዳት ችለናል ።


(ንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ )