የፊርማ ስነስርዓት ሲከወን (ፎቶ; ሲሳይ ጉዛይ)
ሮፍናን "ሐራንቤ" እና "ኖር" የተሰኙ አልበሞች በአንድ ቀን የሚወጡ መሆኑን ከዚህ ቀደም ለጋዜጠኞች መናገሩ ይታወሳል ።
ከሂንከን ኩባንያ ዋልያ ቢራ ጋር ለሚቀጥሉት 18 ወራት በጋራ መስራት የሚያስችሉትን ኤግዚክዩቲቭ ሆቴል ዛሬ የፊርማ ሥነ ስርዓት ላይ ተመልክተናል ።
የሙዚቃ ባለሞያው ሮፍናን 'ስድስት' በተሰኘው የቀደመ የሙዚቃ አልበም አጋሩ ከነበረው የሄይኒከን ኢትዮጵያ ዋልያ ቢራ በአርቲስቱ 'ዘጠኝ' አዲስ አልበም ላይ አጋርነቱን መቀጠሉን አስታውቋል።
በዚህ ሳምንት ከጥር 27 እስከ ጥር 29 በተካሄደ ማስተር ክላስ መርሃ ግብር ድምጻዊዉ ያለውን ልምድ እና እውቀት ለጀማሪ እና ወጣት ሙዚቀኞች ማጋራቱ አይዘነጋም።
ይህ መርሃ ግብር በክልል ከተሞችም እንደሚቀጥል ሮፍናን ለመገናኛ ብዘለሐን ባለሞያዎች ተናግሯል ።
ቀደም ሲል ከአልበሙ ላይ እንደቅምሻ የለቀቀውን ነጠላ ዜማ ከቲክቶክ መተግበሪያ ላይ ወጥቶ ነበር።
ይህንን ተከትሎ ከዩኒቨርሳል ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ድርጅት ጋር ባለው ስምምነት ምክንያት እንደሆነ አርቲስቱ ጠቅሷል።
(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)
