የአቪየሽን ሙዚየም ያስፈልገናል

 ልዩ -ምልከታ




- ፀኃፊ ቃለየሱስ በቀለ (የአቬየሽን ጋዜጠኛ)


ኢትዮጵያ በአቪየሽን መስክ ረጅም ታሪክ ቢኖራትም እስካሁን ይህን ታሪክ የሚያሳይ የአቪየሽን ሙዚየም ባለቤት ለመሆን አልታደለችም ።


ራይት ብራዘርስ የመጀመሪያውን ጢያራ ከፈበረኩ ከ9 አመት በሃላ አውሮፕላን ኢትዮጵያ ገብቷል።


 ሰሞኑን ወደ ሀገርቤት የተመለሰችው ፀሃይ በ1925 እዚሁ የሀበሻ ምድር ተሰርታለች ሌሎች አውሮፕላኖች በፋሽስት ኢጣሊያ ወድመዋል ።


የኢትዮጵያ አየርመንገድ የ78 አመት አኩሪ ታሪክ ባለቤት ነው  በአፍሪካ ህብረት ምስረታ የበኩሉን አስተዋፆ አድርጎል አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት ያስተሳሰረ አየርመንገድ መኾኑ ይታወቃል።


በ1960ዎቹ ጀት አውሮፕላን ለአፍሪካ ያስተዋወቀ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ነበር።


በ1970ዎቹ ቦይንግ 767 አውሮፕላኖችን ገዝቶ በመጠቀም ከአለም ከእስራኤሉ ኤልአል በመቀጠል ሁለተኛው አየርመንገድ ነው።


"767 is coming" የሚለው ማስታወቂያ የማይዘነጋ ነው።


በ2012 የድሪምላይነር አውሮፕላን ባለቤት በመሆን ከጃፖን ቀጥሎ ሁለተኛ ነው።


 ወቅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በርካታ አፍሪካውያን አብራሪዎች እና ቴክኒሺያኖች አሰልጥኗል።


ዛሬ አየርመንገዱ ከአየር ትራንስፖርት አገልግሎት አልፎ የአውሮፕላን እቃዎች እያመረተ ለቦይንግ ኩባንያ በማቅረብ ላይ ነው።


 የኤሮስፔስ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ በመመስረት ሂደት ላይ ይገኛል ።


ቀዳማዊ ግርማዊ ሃይለስላሴ እና The Brown Condor በሚል ቅፅል ስም የሚጠራው አፍሮ አሜሪካዊው ኮረኔል ጆን ሮቢንሰን በኢትዮጵያ የአቪየሽን ኢንዱስትሪ መሰረት መጣላቸውን ይነገርላቸዋል።

 

በንጉሱ ትእዛዝ አየርምንገዱን አሜሪካኖች (TWA) አየር ሃይሉን ስዊድኖች አቋቁሞ ነበር።


 አየር ሃይሉ በአፍሪካ ቀደምት ከሚባሉት ተርታ የሚሰለፍ ነው።


የቀድሞፖሊስ ሰራዊት እና የእርዳታ ማስተባበሪያ እና ማቋቋሚያ ኮምሽን የራሳቸው አውሮፕላን ነበራቸው 


በንጉሱ ዘመን አድማስ የፀረ አረም መርጫ ኩባንያ የግል ነበር  የአስመራው ሜሎቲ ቢራ ፋብሪካ መስራች ሚስስ ሜሎቲ እና ልኡል አስራተ ካሳ የግል አውሮፕላን እና ሄሊኮፐተር ባለቤት ነበሩ።

 

በ1977 እሸት የተሰኘችው የፀረ አረም መርጫ አውሮፕላን በኢትዮጵያ አየርመንገድ ጥገና ማእከል ውስጥ ተገጣጥማለች ።


ይህን ሁሉ ታሪክ ለልጆቻችን ለመጪው የአቪየሽን ባለሙያዎች እና ለቱሪስት የምናሳይበት አንድ የአቪየሽን ሙዚየም ባለመኖሩ ብዙዎቹን ያስቆጫል።


ፀሃይን ለማስመለስ ጥረት ሲጀመር ስትመጣ የትነው የምትቀመጠው የሚለው አንዱ የመወያያ አጀንዳ መኾን ነበረበት የሚሉ ባለሞያዎች አሉ።


የኢትዮጰያ አየርመንገድ የኢትዮጵይ ሲቭል አቪየሽን የኢትዮጵያ አየርሃይል እና የትራንስፖርት ሚኒስቴር ተባብረው ቦይንግ እና ሌሎች አጋሮች እገዛ ጠይቀው የአቪየሽን ሙዚየም ሊገነቡ ይገባል እየተባለ ነው።


 በየሰርቻው ተጥለው ዝናብ እና ፀሃይ የሚፈራረቅባቸው ታሪካዊ አውሮፕላኖች ተሰብስበው በተገቢው ቦታ ይቀመጡ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።

[ንጋት ፕሬስ]