የስፓርት አውደ ርዕይ በአዲስአበባ ከተማ ሊካሔድ ነው



       photo; ጋዜጣዊ መግለጫ በሚሰጥበት ወቅት ( ፎቶ ሲሳይ ጉዛይ)


 በኤግዚቢሽን ማእከል ለሶስት ቀናት የስፓርት አውደርእይ ሊካሔድ መኾኑን ተነግሯል ።


መርኃ ግብሩ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከበርኖስ ማስታወቂያና ኢንተርቴመንት ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።


መርሐግብር አስመልክቶ በአዲስአበባ ከተማ ሳሬም ሆቴል ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።


 መግለጫ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ   ዳዊት ትርፉ  ይህ ፌስቲቫል  በከተማ ደረጃ የመጀመርያው የስፓርት ፌስቲቫል መኾኑን ተገልጿል።


ከዚህ ቀደም በዚህ መልኩ እንዳልተደረገ እና ለስፖርቱ ማደግ እና ለስፖርት ኢንቨስትመንቱ ከፍተኛ አስተዋጾ እንደሚኖረው ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ።


 ፌስቲቫሉና አውደ ርእዩ የፊታችን አርብ ከየካቲት 8-10 ለሶስት ቀናት የሚቆይ ነው ተብሏል።


 በፌስቲቫሉም 36ቱም የስፖርት ፌዴሬሽኖች ይገኛሉ  መባሉን ሰምተናል ።


በተጨማሪም  የተለያዮ በስፖርቱ ዙሪያ የሚሰሩ  ጂምናዝየም፣ የስፖርት ልብስ የሚሸጡ እንዲሁም ሌሎች የሚሳተፉ ሲሆን የተለያዮ አንጋፋ ክለቦችም  ለራሳቸውን  ያስተዋውቃሉ ተብሏል ።


 የመግቢያ ዋጋ 50 ብር መኾኑን ተረድተናል ። 


(ንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)



                      -Advertisements-